2010-01-11 14:04:41

የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት፦ የጥሪ ሳምንት


በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ከትላትና እሁድ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የጥሪ ሳምንት መከፈቱ ተገልጠዋል። የአሜሪካ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በዚህ ሳምንት ስለ ጥሪ የምታስተነትንበት ስለ ጥሪ ሀሳብ RealAudioMP3 እና የተጠሩት ብርታት እንዲያገኙ የሚጸለይበተ ሳምንት መሆኑ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የውሉደ ክህነት ኮሚቴ ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ሲን ኦማለይ አስታወቁ።

በዚህ የክህነት ዓመት ምክንያት ወጣቶች በጥልቀት እራሳቸውን በማዳመጥ በእምነት በርትተው እራሳቸው አውቀው እራሳቸው ሆነው እንዲኖሩ እንዲጸለይላቸው፣ ሌላው ከመምሰል የወቅቱ ፈተና ተላቀው እራሳቸውን መስለው እና ሆነው ለመኖር እንዲችሉ በዚህ መስክ ይበረቱ ዘንድ የሚጸለይበት አስተምህሮ የሚሰጥበት ሳምንት መሆኑ ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. ጥር 14 ቀን 2009 ዓ.ም. የተለያዩ በአሜሪካ የሚገኙት የልኡካነ ወንጌል ማህበራት እና ሰበካዎች በመተባበር ስለ ጥሪ የሚመለከተ ስነ ባህላዊ መግለጫ ይቀርባል። በዚህች አገር የጥሪ ሳምንት እ.ኤ.አ. በ 1976 ዓ.ም. ተጀምሮ በየአመቱ የአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሚያቀርበው መርሃ ግብር መሠረት የሚካሄድ መሆኑም ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.