2010-01-11 13:58:04

የቅድስት መንበር ፍርድ ቤት


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ በቫቲካን ያስተዳዳሪ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የቅድስት መንበር የፍርድ ቤት ዓመታዊ የሥራ ሂደት RealAudioMP3 ማስጀመራቸው ተገለጠ።

ብፁዕነታቸው በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት ባሰሙት ስብከት፣ ሕግና ፍትህ ስምምነት እና ሰላም ለማስፈን የሚከናወን በመሆኑ ይህ ዓላማ አለ እግዚአብሔር የማይደረስ እና የማይጨበጥ መሆኑም የሚያረጋግጥ ግንዛቤ ከፍ እያለ መምጣቱን አብራርተዋል። ቀጥሎ በተካሄደው ጉባኤ የቅድስት መንበር ፍርድ ቤት የሕግ ሥራ አስፈጻሚ ጠበቃ ኒኮላ ፒካርዲ እ.ኤ.አ. የፍርድ ቤቱ የ 2009 ዓ.ም. ሥራ ክንዋኔ የሚያብራራ ሰነድ በማቅረብ እንዳመለከቱት፣ የቫቲካን የሕግ እና ፍትሕ ሥርዓት ብቃት ያለው ሚዛኑ የጠበቀ አመርቂ መሆኑ ሲታወቅ፣ በዚህ አጋጣሚም የቫቲካን የሕግ እና ፍትሕ ጉዳይ ጽ/ቤት እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ምሥረታ 80 ዓመት ማስቆጠሩንም አስታውሰው በነዚህ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 474 የብሔር ክሥ እንዲሁም 446 የቅጣት ክሶች ጉዳይ መመልከቱ እና ውሳኔ መስጠቱንም ገልጠው፣ በዓመቱ ውስጥ የሚቀርቡት የብሔርም ሆነ የቅጣቱ ክሶች ጉዳይ በቀረቡበት ዓመት ውስጥ እንደሚሰጥ እና የሥራ ውዝፍ እንደሌለም ገልጠው፣ የቫቲካን ፍርድ ቤት በቂ የሰው ኃይል ያለው የሥራ ጥራት እና ብቃት እጅግ እያሻሻለ መምጣቱንም አብራርተው፣ የኤኮኖሚ እና የማኅበራዊ መብት እና ግዴታ በተመለከተ የቫቲካን ሠራተኞች ጉዳይ የሚከታተለው የፍርድ ቤት ጽ/ቤት ግን የፍርድ ቤት ሥራ እያከበደው መሆኑ በመጥቀስ የሠራተኛ ጉዳይ የሚመለከት በቂ መመሪያ እና ሕግ ያለ ቢሆንም ጽ/ቤቱ ይኸንን የሚመለከተው ሥራውን ማሳየል እንደሚያሻም ገልጠዋል።

የሕግ እና ፍትሕ ጉዳይ በሰብአዊ አግባብ ባለው አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ከወንጌል የሚመነጭ አግባብ ባለው አስተሳሰብ የተሸኘ መሆን እንዳለበት ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ባሰሙት ስብከት በመጥቀስ፣ ስለዚህ የክርስቶስን ፍቅር በመከተል ይህ ፍጽሙ ፍቅር የማስፋፋት ብቃት ያለው በእምነት ላይ ጸንቶ ሕግ እና ሥርዓት የሚያስፈጽም ፍርድ ቤት መሆን አለበት እንዳሉም ከቅድስ መንበር የተላለፈልን ዜና ያረጋገጣል።








All the contents on this site are copyrighted ©.