2010-01-11 14:13:43

የቅስድት መንበር የዜና እና የማህተም ክፍል ርእሰ አንቀጽ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 አበክረው ለኢአማኒያን እና እንዲሁም ባለፈው እሁድ በላቲን ሥርዓት በተከበረው በዓለ ግልጸት የከዋክበት ተመራማሪዎች ወደ ቤተ ልሔም ያደረጉት ጉዞ መሠረት በማድረግ በሰጡት RealAudioMP3 አስተምህሮ፣ አለ ምንም ጅምላዊ ቅድመ ፍርድ ትሕትና በተካነው እና ክፍት በሆነ አእምሮ አማካኝነት እውነትን መሻት አስፈላጊ ነው ያሉትን ሀሳብ የቅድስት መንበር የዜና እና የማህተም ክፍል ተጠሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ላቀረቡት ርእሰ አንቀጽ መሠረት በማድረግ፣ በአሁኑ ወቅት እንደሚታየው የሰው ልጅ በራሱ በመተማመን በራስ መቻል ላይ ብቻ መጽናት እውነትን ለመፈለግ ለሚያደርገው ጥረት የተሟላ ባለ መሆኑ ምክንያት አእምሮ ትሕትና ያልተካነ እና ክፍት ባለ መሆኑ ምክንያት በእምነት እና በምርምር መካከል ምንም አይነት ግኑኝነት እንደሌለ ተደርጎ የሚከናወን እውነትን የመሻት ሂደት ከእውነት እንደሚያርቅ በማብራራታ፣ የከዋክብት ተመራማሪዎች ይኸንን እንዳረጋገጡ በመጥቀስ፣ በሰው አእምሮ ሊገመት የማይቻለውን ትልቅ እና ድንቅ የሆነውን እውነት ለማወቅ ለማመን የሚያበቃ ትክክለኛ ብርታት አስፈላጊ ነው እንዳሉም ኣባ ሎምባርዲ በማስታወስ በእምነት እና በምርምር መካከል ያለው ግኑኝነት ርእሰ ጉዳይ በማድረግ የሚካሄደው ጥናት ከጥንታዊው የክርስትና የጥናት ሂደት ጀምሮ የነበረ ወቅታዊነት ያለው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመደጋገም ስለ ጉዳዩ ሰፊ አስተምህሮ በመስጠት የሥልጣናዊ ትምህርታቸው መሠረትም መሆኑ ጠቅሰው፣ እ.ኤ.አ. ያለፈው ዓመት በታሪክ የተፈጸሙት አበይት የስነ ምርምር ክንዋኔዎች የስነ ምርምር ውጤቶች እና የስነ ከዋክብት የምርምር ዓመት ተብሎ ተሰይሞ እንደነበርም ኣባ ሎምባርዲ በማስታወስ ቅዱስ አባታችን በተለያዩ መልእክቶቻቸው እና በደረሱዋቸው አዋዲ መልእክቶቻቸው ጭምር በማጥቀስ ለስነ ምግባር እና የሰው ልጅ እድገት መሠረታዊ ጥያቄዎች በመዳሰስ በማስረዳት እንደ የከዋክብት ተመራማሪዎች ቤተ ልሔም ደርሰው እውነትን አውቀው እና ከእውነት ጋር ተገናኝተው ያገኙት እፎይታ የሰው ልጅ እውነትን ለማወቅ ለሚያደርገው ጥረት አብነት ናቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.