2010-01-11 14:02:59

ከሙዚቃ አቀነባባሪነት ለክህነት ጥሪ


ኣባ አልዶ ባዛን የአጎስጢኖሳውያን ማኅበረ አባል ካህን ለመሆን በዚህ ማኅበር ገብተው ክህነት ከመቀበላቸው በፊት በአንድ የራዲዮ ጣቢያ የሮክ እና ፖፕ ሙዚቃ አቀነባባሪ ላድማጮች የምርጫ ዘፈኖችን በማቀነባበር እና RealAudioMP3 በማቅረብ ይሠሩ እንደነበር ሲገለጥ፣ ዛሬም ክህነት ተቀብለው በዚህ በሙዚቃ ዘርፍ ያላቸው እውቀት እና ችሎታ አማካኝነት ከወጣት የህብረተሰብ ክፍል ጋር ለመወያየት እንደሚጠቀሙበት፣ የክህንት ዓመት ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ፣ ስለ ክህነት ጥሪያቸው ሲገለጡ፣ የከፍተኛ ሁለተና ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በፍልስፍና እና ቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ ተመዝግበው በግል ትምህርታቸውን ጀምረው፣ በትርፍ ጊዜያቸውም በሙዚቃው መድረክ የሮክ እና ፖፕ ሙዚቃ የዘፈን ምርጫ በሚያቀርበው ረድዮ ተጠቅጥረው የሚመረጡት ሙዚቃዎችን በማቀነባበር ሲሠሩ፣ በመንበረ ጥበብ በፍልስፍና ትምህርታቸው የቅዱስ አጎስጢኖስ የፍልስፍና መንፈሳዊ እና ቲዮሎጊያው ጽሑፎች ጠልቀው በማወቅ እጅግ ማርኳቸው የዚህ ቅዱስ ተከታይ ለመሆን በውስጣቸው ለተሰማቸው ጥሪ መልስ ለመስጠት በአጎስጢኖሳውያን ማኅበር በመግባት የፍቅር ግሽበት በሚታይበት ዓለም የተስፋ አብሳሪ ለመሆን በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በሚገባው ባህል ቀርቦ የዚህ ፍጽሙ ተስፋ አማኝ እንዲሆን መደገፍ አብሮት መጓዝ በሚለው እቅድ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውም አመልክተዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለምበዚህ እ.ኤ.አ. ስኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የከፈቱት የክህነት ዓመት ምክንያት በማድረግ የህንድ ውሉደ ክህነት የክርስቶስ ዱካ መከተል በተሰኘው መሪ ቃል ተሸኝቶ በቅድስት መሬት መንፈሳዊ ንግደት ለማካሄድ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እቅድ መወጠኑ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.