2010-01-09 10:40:27

የቤተ ሰብ ዓቢይ በዓል በእስፓኛ ማድሪድ ላይ ተከበረ.


በእስፓኛ የርእሰ ከተማ ማድሪድ ሀገረ ስብከት ትናትና የቅድስት ቤተሰብ በዓል ያዘጋጀ እና ያከበረ ሲሆን በማድሪ ከተማ በሚገኘው ሊማ አደባባይ አንድ ሚልዮን ህዝብ ተሰብስቦ በዓሉ ማክበሩ ከቦታው የገኘ ዜና አስታውቀዋል።

እኤአ በ1982 ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማድሪ በጐበኙበት ግዜ

የሰው ልጅ መጻኢ ዕድል በክርስትያናዊ ቤተሰብ የተመሰረተ ነው ብለው ነበር።

በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ወደ ማድሪድ የተላኩ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዓረፍተ ነገር በማስታወስ በማድሪድ ከተማ ሊማ አደባባይ ለተሰበሰበ አንድ ሚልዮን ህዝብ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሰላምታ አድርሰው የኤውሮጳ ቤተ ሰቦች ግላዊ ሳይሆኑ ህዝባዊ መሆናቸው ጠቁመው ፡ የኢየሱስ ሕጻን ፍቅር ያውጃሉ ማለታቸው ከማድሪድ የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

በቅድስት መንበር የቤተሰብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ብፁዕ ካርዲናል ኤንዮ አንቶነሊ የምእመናን ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁዕ ልካርዲናል ስታንስላው ሪኤልኮ የፖላንድ የጳጵሳት ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሚካሊክ የኮር ኡኑም ጳጳሳዊ ማኅበር ፕረሲዳንት ብፁዕ ካርዲናል የሲፍ ኮርደስ በጀርመን የበርሊን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ገኦርግ ስተርጺስኪ በዚሁ ማድሪድ ላይ የተከበረ የቅድስት ቤተሰብ ዓቢይ በዓል ተገኝተው ክርስትያናዊ ቤተሰብ ትኩርተት የሰጠ ንግግር ማድረጋቸው ዜናው ለጥቆ ገልጠዋል።

የትምርተ ክርስቶስ ይዘታ ተንታኝ እና በዓሉ ከየምድሪድ ሀገረ ስብከት በመተባበር ያዘጋጁት ኪኮ አርጉኤሎ በዚሁ የሊማ አደባባይ የቤተ ሰብ ቀን ለተሰበሰበ በአንድ ሚልዮን የሚቁጠር ህዝብ እንደገለጹት ፡ ኤውሮጳ የምትድነው በክርስትያናዊ ቤተ ሰብ ብቻ ነው።

በየእስፓኛ ርእሰ ከተማ በሊማ አደባባይ የቤተ ሰብ ቅዱስ ዕለት ምክንያት በበርካታ ካርዲናላት እና ጳጳሳት ተሸኝተው መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት የከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ማሪያ ሮኾ ቫረላ በ2011 ማድሪድ ላይ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንደሚከናወን አስታውሰው ይህም ከክርስትናዊ ቤተሰብ የተሳሰረ ሌላ ዓቢይ በዓል እንደሚሆን ማመለከታቸው አብሮ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ቤተ ሰብ የናዝሬት ቤተሰብ ምስል መሆኑ እና ህጻናት ሕሙማን አካለ ስንኩላን ከዚህ ከናዝሬት ቤተሰብ ማለት ከዮሴር ማርያም ኢየሱስ የሕወት ስጦታ እንደሚቀበሉ ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ማሪያ ሮኾ ቫረላ መግለጻቸው ተነግረዋል።

መንግስታት ሁሉ የቃል ኪዳን ተቋሞች እንዲጠብቁ እና እንዲከንባከቡ ይጠራሉ ያሉት የማድሪድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ማሪያ ሮኾ ቫረላ ኤውሮጳ ውስጥ የሚታየው የቤተሰብ መነጣጠል እና ጽንስ የማስወረድ ድርጊት አሳሳቢ መሆኑ ማስረዳታቸው ይህ ከማድሪድ የመጣ ዜና አመልክተዋል።

ኤውሮጳ አለ ክርስትያናዊ ቤተ ሰብ ልጆች እና ፍቅር አልባ በቀረች ነበር ያሉት ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ማሪያ ሮኾ ቫረላ ክርስትያናዊ ቤተ ሰብ እንዲያብብ ተመኝተዋል በማለት ዜናው በተጨማሪ ገልጠዋል።

ከተለያዩ የኤውሮጳ ሀገራት በዚሁ የቅድስት ቤተሰብ ቀን ለመገኘት ወደ ማድሪድ መጐረፋቸው ያመልከተ ዜና በብዛት የጣልያን የፖላንድ የፈረንሳ እና ጀርመን በብዛት በዚሁ በዓል ተሳታፊ መሆናቸው ታውቆዋል ።

የኤውሮጳ ክርስትያናዊ እሴቶች እና ባህሎች ለመታደግ የኤውሮጳ ክርስትያኖች ያለሰለሰ ጥረት እንድያካሄዱ በዚሁ በዓል መጠራታቸውም የማድሪድ መገናኛ ብዙኀን ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.