2010-01-09 10:40:41

በነዲክቶስ የአልባንያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ተቀብለው አነጋገሩ.


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የአልባንያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሊ በሪሻ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ እና የአልባንያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሊ በሪሻ በቅድስት የድስት መንበር እና አልባንያ ወቅታዊ ግንኙነት የምዕራባዊ ባልካን ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸው መግለጫው አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሚቀጥለው ዓመት 2010 እኤአ አልባንያ ብፅዕት ተረሳ ዘ ካልኩታ የተወለደችበት መቶኛ ዓመት መሠረት በማድረግ አልባንያ እንዲጐበኙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳል በሪሻ ቅድስነታቸውን መጋበዛቸው መግለጫው ገልጸዋል።

የድሆች እናት ብፅዕት ተረሳ ዘካልኩታ ከአንድ መቶ ዓመት በፊት አልባንያ ውስጥ ከአንድ ካቶሊካዊ ቤተሰብ መወለዳቸው የሚታወስ ነው ።

የአልባንያ መንግስት ጠቃላይ ሚኒስትር ሳሊ በሪሻ ከየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና ከየውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ከሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር በመገኛኘት ሐሳብ መለዋወጣቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.