2010-01-09 10:40:07

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በቅድስትመንበር የተመደቡ የቱርክ አዲስ አምባሳደር የሲመት መልእክት ተቀበሉ.


በቅድስት መንበር የተመደቡ የቱርክ መንግስት አዲስ አምባሳደር ኬናን ጉርሶይ ትናንትና ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሲመት መልእክት ማቅረባቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ አዲስ የቱርክ አምባሳደር ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ እንዳመለከቱት ፡ በተለያዩ ሃይማኖቶች ሁነኛ ውይይት እንዲካሄድ የቱርክ መንግስት ሀገሪቱ ውስጥ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንን ሕጋዊ እውቅና እንድትሰጥ የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሔ እንዲገኝለት ጥረት ማካሄድ ያሻል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በ2006 እኤአ በቱርክ ላይ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አስታውሰው ፡ የቱርክ ካቶሊካዊ ማኅበረ ሰብ ለሀገሪቱ ኅበረተሰብ እድገት የሚያደርገው አስተዋጽኦ መልካም መሆኑ መግለጻቸው መግለጫው ገልጸዋል።

በቱርክ የክርስትያን ማኅበረ ሰብ አንስተኛ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ፡ በክርስትያኖች እና ሙስሊሞች መካከል የሚካሄደው ውይይት እና ትብብር ለሰላም እና እድገት ዓቢይ እገዛ መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቅድስት መንበር ለተመደቡት የቱርክ መንግስት አምባሳደር መግለጻቸው ተመልክተዋል።

የቱርክ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማስፈን የበኩልዋ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ታደርግ ዘንዳ የጠየቁት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ቱርክ የምስራቅ እና ምዕራብ ድልድይ መሆንዋ ማመልከታቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስገንዝበዋል ።

ታሪክ እንዳስየው ሁሉ የግዛቶች ይገቡኛል ግጭት እና በጐሳዎች መካከል የሚከሰቱ አለመጣጣሞች ሚዛን የጠበቀ የሁለቱ ወገኖች ፍላጎት ሐሳብ ግምት ውስጥ ገብተው ለሰላማዊ ድርድር በማምጣት መፍትሔ ሊገኝ ይችላል ፡ ወሳኙ ሰብአዊ ክብር መጠበቅ እና ለመቀራረብ መፈለግ መሆኑ ቅድስነታቸው በተጨማሪ ለአዲስ የቱርክ አምባሳደር መግለጣቸው ተመልክተዋል።

አያይዘውም ቅድስት መንበር በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማስፈን እና ክልላዊ ዕርቅ እንዲገኝ ዲፕሎማሲ ጨምሮ የተቻላትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናው መግለጻቸው ታውቆዋል።

በቱርክ ኢስጣምቡል ላይ የቅስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ሆነው ለረጂም ዓመታት የሰሩ እና ኃላም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰየሙት ዮሐንስ ሃያ ሶስተኛ በቅስት መንበር እና በቱርክ

ጥኑ ግንኙነት እንዲኖር መሠረት ማስቀመጣቸው ቅድስነታቸው ማስታወሳቸው ትገልጠዋል።

የቫቲካን እና የቱርክ ጥኑ ግንኙነት ባለበት ቀጥሎ በበለጠ ለማተከርም ሁለቱ ወገኖች ጥረታቸው እንድያጠናክሩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ያላቸውን ተስፋ በቅድስት መንበር ለተመደቡት የቱርክ አዲስ አምባስደር ኬናን ጉርሶይ እንደገለጡላቸው ተያይዞ ተመልክተዋል።

የቁስጢንጢንያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባርቶሎመዮ አንደኛ በዓለም ዙርያ ሰላም እንዲሰፍን እና የአከባቢ እንክብካቤ እንዲድረግ ያላቸውን ሐሳቢነት የክርስትያኖች አንድነት እውን እንዲሆን ያላቸውን ከፍተኛ ምኞት እና ለዚሁ የሚያደርጉት ያለሰለሰ ጥረት አሞግሰው ማመስገናቸው የቫቲካን መግለጫ ዘግበዋል።

በመጨርሻም የቱርክ መንግስት ባለሥልጣናት ሀገሪቱ ውስጥ በቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ዓመት ግዜ ከሐዋርያው በተሳሰሩት መካኖች በሰላም ሥርዓተ አምልኮ እንዲከናወን እና በየቅዱስ ጳውሎስ ዓመት ምክንያት ምእመናን ወደ ሀገሪቱ አለማኝኛውም እንቅፋት ገብተ በነፃ

እንዲንቀሳቀሱ ያሳዩት ፈቃደኝነት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ማመስገናቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.