2010-01-08 14:36:24

ኮንጎ


በዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ሰሜናዊ እና ደቡባዊ የኪቩ ክልል ያለው ሁኔታ በተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት የታዛቢ አካላት በ 2009 ዓ.ም. ባቀረቡት ሰነድ ያለም አቀፍ ማኅበረሰብ እና መንግሥታት የዚህ ክልል RealAudioMP3 ሁኔታ ችላ ሊለው እንደማይገባው ማሳሰቡ ሰላም ለኮንጎ የተሰኘው ዘመቻ ያነቃቃው የሳቨሪያኒ ልኡካነ ወንጌል ማኅበር በማስታወስ፣ ይህ ረዥም እንዲሁም አሰቃቂው ግጭት እና አመጽ በሰው እና በንብረት ላይ አቢይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ በመግለጥም፣ ለዚህ ክልል ሕዝብ ድጋፍ እና ትብብር ይቀርብ ዘንድ ማሳሰቡ ፊደስ የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።

የክልሉ ግጭት ጎሳዊ ግጭት ነው እየተባለ የሚሰጠው ትንታኔ የሳቨሪያኒ ልኡኣካን ማኅበር መሠረት የሌለው ነው በማለት፣ የግጭቱ መንስኤ በክልሉ ያለው የተፈጥሮ ሃብት ለመቆጣጠር እና የማዕድን ሃብት በሕገ ወጥ መንገድ እና ኃይል ተገን በማድረግ የሚደረገው የአገር እና የሕዝብ ሃብት ብዝበዛ የቀሰቀሰው ጉዳይ ነው እንዳለምም ፊደስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት እና ታላቋ ብሪታኒያም ጭምር በዚህ ክልል ላለው ግጭት ዕልባት ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ የተያያዙት የኮንጎ የተፈጥሮ ሃብት ሕገ ወጣዊው ብዝበዛ ይገቱ ዘንድ ተጽእኖ ማድረግ፣ ሰላም ለማስጠበቅ በሚል አላማ በአበይት ኃይቆች ክልል የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ማሰማራት ለሌላ ተጨማሪ አቢይ ችግር ምክንያት መሆኑ በመግለጥ ክልል ወታደራዊ ጦር ሠፈር የሚያደርግ ተልእኮው እንዲቋረጥ፣ በዚህ ክልል የሚታየው አምባገነናዊ ፖሊቲካዊ ሥርዓት ማስወገድ ለክልል ሰላም መረጋገጥ መሠረት መሆኑ የሳቨራውያን ልኡካን ማህበር በማብራራት ይኸንን ሀሳብ የሚያብራራ መልእክት ለተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ጭምር ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.