2010-01-08 14:37:18

ቤተ ክርስትያን በሱዳን


የሰላም ፍላጎት በማስተናገድ እርቅ ማነቃቃት በሚል መሪ ሃሳብ በሱዳን በባህር አል ጋዛል ክልል የዋኡ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ሩዶልፍ ዴንግ ማጃክ ባለፈው እሁድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የቀረበውን መሥዋዕተ ቅዳሴ RealAudioMP3 መርተው ባሰሙት ስብከት የሰላም ጥሪ በማቅረብ፣ 2010 ዓ.ም. የሰላም ጉባኤውች ግኑኝነቶች የመሳሰሉ መርሃ ግብሮች ብቻ የሚከናወንበት ሳይሆን፣ ሰላም የሚረጋገጥበት ዓመት ይሆን ዘንድ በማሳሰብ፣ የሱዳን ርእሰ ብሔር ኦማር ሃሳን አል በሺር እና ምክትላቸው ሳልቫ ኪሪ ማያርዲት በአቢየይ የደቡብ ሱዳን ህዝብ የራስ ዕድል በራሥ የመወሰኑ መብት በሕዝብ ውሳኔ መልስ ያገኝ ዘንድ መስማማታቸው ብፁዕነታቸው በመጥቀስ አመስግነው፣ የመንግሥት አካላት ሱዳንን ለእግዚአብሔር በመስጠት ሕዝብ ለሰላም እና ለእርቅ ይተጋ ዘንድ በዚሁ መስክ ተቀዳሚው ሚና እንዲጫወቱ አደራ ብለዋል።

እ.ኤ.አ. ጥር 2011 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን ህዝብ ርእሰ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀነ ቀጠሮ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር አል በሺር በመጥቀስ፣ ዕለቱ የሱዳን አንድነት የሚመሰክር እና የሚያጸና እለት እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ከወዲሁ በማሳወቅ፣ ሕዝበ ውሳኔ ለአንድነት እንጂ ለመከፋፍል ለመለያየት የሚገፋፋ እንዳይሆን መንግሥታቸው ሰላም እና ማረጋጋት ተቀዳሚ ዓላማው በማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ማሳወቃቸውም ተገልጠዋ።







All the contents on this site are copyrighted ©.