2010-01-08 14:33:59

ቤተ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሁሉም ክፍት ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላንትና ቫቲካን በሚገኘው በክለመንቲና አዳራሽ በቫቲካን ከተማ ክልል ጸጥታ እና ደህንነት ለሚያረጋገጡ የኢጣሊያ የቅዱስ ጴጥሮስ ክልል ጸጥታ አስከባሪ ወታደራዊ ኃይል RealAudioMP3 አዛዦች እና አባላትን ተቀብለው አነጋገሩ።

ቅዱስ አባታችን የጸጥታ አስከባሪ ወታደራዊ ኃይል አባላት ተቀብለው ባሰሙት መልእክት፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሁሉም ለአማኞች እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ ክፍት መሆኑ በማረጋገጥ፣ በዚህ በተካሄደው ግኑኝነት የኢጣሊያ የወታደራዊ ፖሊስ አዛዥ ጀነራል ለዮናርዶ ጋሊተሊ እና የሮማ ክፍለ ሃገር የወታደራዊ ፖሊስ አዛዥ ጀነራል ቪቶሪዮ ቶማሶነ መገኘታቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሚመጡት መንፈሳውያን ነጋድያን ለተለያዩ ይፋዊ ግኑኝነት ጭምር ወደ ቅድስት መንበር ለጉብኝት የሚመጡት እንግዶች እና ባለ ሥልጣናት ጸጥታ እና ደህንነት ለማስከበር የወታደራዊ ፖሊስ አባላት የሚሰጡት አገልግሎት በመጥቀስ ቅዱስነታቸው አመስግንስዋል። የቅዱስ አጽም ያረፈበትን ቅዱስ ሥፍራ ለመሳለም ከተለያዩ የአለማችን ክልል የሚጎርፈው ነጋድያን ቅዱስ ዓላማ እንዳይሰናከል በክርስቶስ ወንድሞችን በእምነት እንዲጸኑ ለማድረግ ኃላፊነቱ ለተሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ር.ሊ.ጳ. ጋር ለመገናኘት የሚደጉት እቅዶች የተዋጣለተ ይሆን ዘንድ የሚሰጡት አገልግሎት እጅግ አመርቂ መሆኑም ጠቅሰው፣ መንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሁሉም ክፍት የሁሉም ቤት ነው ብለዋል።

የጸጥታ ኃይል አባላት በትህትና እዩሉኝ ሳይሉ ትእግሥት በተሞላው ተልእኮ ነጋድያን አማኞች እምነታቸው ለመግለጥ የሚፈጽሙት መንፈሳዊ መርሃ ግብር ግቡን እንዲመታ የአካባቢ ጸጥታ እና ደህንነት በማስጠበቁ ረገድ የሚሰጡት አስተዋጽኦ ንቃት የሚጠይቅ አቢይ ኃላፊነት መሆኑም ቅዱስነታቸው በመግለጥ ይህ እቅድ እግዚአብሔር እንዲባርከው ተማጥነው፣የጸጥታ ኃይል አባላት ቅን ሃሳብ ጌታ እንዲያቀናላቸው ቤተሰቦቻቸውንም እንዲባርክ በሚሰጡት አገልግሎት ጌታ ጠብቆ እንዲመራቸው ጸልየው ቡራኬ በመስጠት ማሰናበታቸው ከቅድስት መንበር የተላለፈልን ዜና አረጋገጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.