2010-01-06 12:44:52

በዓለ ግልጸት/አስተርእዮቱ


በላቲን ሥርዓት ዛሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአሕዛብ የተገለጸበት ዕለት የሚከበር ሲሆን፣ ይህ ዓቢይ በዓል በጨለማ ላይ ድል የነሳ ዘወትር ሕይወታችንን የሚያበራውን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን እንቀበል RealAudioMP3 በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዓሉ ምክንያት በማድረግ እ.ኤ.አ. ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት በመግለጥ፣ ዕለቱ እንደ ጠቢባኑ ማለትም የከዋክብት ተመራማሪዎች በምሥራቅ ባዩት ኮከብ ተመርተው ወደ እየሩሳሌም መጡ የተወለደው ኢየሱስ ክርቶስ የት ነው፣ ለእርሱ ልንሰግድለት መጥተናል በማለት የተከተሉት መንገድ ዛሬ የእኛ መንፈሳዊ ሰብአዊ ገጠመኝ ይሁን፣ እንደእነርሱ የድህነታችን መድረሻ ወደ ሆነው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቅና፣ ወደ እርሱ እንሂድ፣ የዛሬ 2 ሺሕ ዓመት በፊት የከዋክብት ተመራማሪዎች ጉዞ ድህነትን የሚሹ የነጋድያን አሕዛብ ምልክት ነው፣ እያንዳንዳችን ወደ ድህነት የምናደርገውን ጉዞ ያመለክታሉ፣ የሚመራ ኮኮብ ለብቻው በቂ አይደለም ተመራማሪዎቹ ለሐቅ ክፍት ስለ ነበሩ እንጂ የመራቸው ኮኮብ ለብቻው በቂ አይደለም፣ በዓለ ግልጸት የነጋድያን ክዋኔ የሚያመለክት እርሱም የሕይወት ትርጉም መነሻ እና መድርሻ የሆነውን ለመፈለግ የሚደረግ ጉዞ ማለት ሲሆን፣ የመድረሻው ነጥብ ክርስቶስ ነው እንዳሉ የሚዘከር ነው።

እንዲሁም ጥር 6 ቀን 2009 ዓ.ም. በዓሉ ምክንያት በማድረግ ባሰሙት ስብከት፣ የክርስቶስ ብርሃን ምንም እንኳ ድቅድቅ ያለ ጨለማ ብርሃንን የሚከድን ጥላ ቢያጋጥምም ቢኖርም የክርስቶስ ብርሃን እንዳያበራ አያግደውም፣ ስለዚህ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ቀውሶች በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች ደመ አፋሻሽ ጥላቻ እና አመጽ፣ እኔ ባይነት፣ ራስ ወዳድነት ሰው የእግዚአብሔር ቦታን ለመተካት ለራሱ የራሱ እግዚአብሔር ለመሆን የሚገፋፋ ፈተና፣ ቤተሰብን የሚበታትን የሕይውት ባህል የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚቀናቀን ፈተና ቢጋረጥም በክርስቶስ የሚያምን ሁሉ ተስፋ አይቆርጥም።

በዓለ ግልጸት ከመደናገር ለመረዳዳት ከመበታተን እና ከመለያየት ለመቀራረብ እና ለመታረቅ የሚገፋፋን ኃይል ነው በማለት ከበዓለ ጰራቅሊጦስ ጋር ያለው ተስምሳይነት አብራርተው እንደነበር የሚዘከር ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.