2010-01-04 16:03:12

የክህነት ዓመት


የፍራንቸስካውያን ማኅበር አባል ወንድም አንጀሊኮ ቦስኬቶ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በመከበር ላይ ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት፣ በድረ ገጽ በኵል የሚከናወኑት ግኑኝነቶች በመጠቀም ወንጌል RealAudioMP3 በማስፋፋት እና በተለይ ደግሞ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል የዚህ አዲስ እና ከቀን ወደ ቀን በማደግ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙሃን መሣሪያ ተጠቃሚ በመሆኑ፣ ይህ ግኝት ለጸረ ሕይወት እና ለኢሞራላዊ ተግባሮች መጠቀሚያ የሚያደርጉት የተለያዩ የወንጀል ቡድኖች ለሚያስፋፉ የሐሰት ትምህርቶች ተጠቂ እንዳይሆን የሚያንጽ ባህል በማስፋፋት ረገድ አቢይ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ግብረ ገብ እና ሥነ ምግባር ለሕይወት ጥበቃ ወሳኝ መሆኑ በማስተማር ተልእኮ ተጠምደው እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ስበኩ የሚለው የወንጌል ቃል መሠረት፣ ቅርብ ላለው ብቻ ሳይሆን እሩቅ ላለው ሄዶ በማግኘትም ይሁን፣ በድረ ገጽ በኩል ጭምር በመገናኘት የሕይወት ቃል ማብሰር አስፈላጊ መሆኑ በመግለጥ፣ ድረ ገጾች በመጠቀም በማወያያ በሮች በኩል ከተለያዩ ወጣቶች ጋር በመገናኘት የተለያዩ መሠረታውያን ጥያቄዎችን በማንሳት በማዳመጥ፣ መልስ በመስጠት ብቻ ሳይሆን፣ መልስ የሆነውን በማቅረብ፣ ክርስትና መልስ ሳይሆን መልስ የሆነውን አካል የሚያቀርብ መሆኑ በዚሁ ረገድ አቢይ ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ እየፈጸሙ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል። እያንዳንዱ ቁምስና የራሱ ድረ ገጽ በመሥራት በዚህ ዓይነት አገልግሎት ይጠመድ ዘንድም በማሳሰብ፣ ቤተ ክርስትያን የሚመጣው ብቻ ሳይሆን ከቤተክርስትያን ርቆ የሚገኘውንም ጭምር በዚህ አዲስ የቴክኖሎጂ መሣሪያ በመጠቀም፣ ቀርባ በማወያየት እና በማስተማር ከተለያዩ ዘርፈ ብዙ አደጋዎች ለማዳን ይቻላል። ስለዚህ ይህ ዓላማ በሁሉም ሰበካዎች ይነቃቃ ዘንድ አደራ ካሉ በኋላ፣ ካህነት የዚህ መሣሪያ የቅርብ እና ጥልቅ እውቀት እንዲኖራቸው እና ከጊዜ ጋር የሚሄድ ሕንጸት በማግኘት ካለው እና እየተስፋፋ ከሚሄደው ማንኛውም ዓይነት ባህል ጋር በመወያየት ወቅታዊነት ያለው ስብከተ ወንጌል እግብር ላይ እንዲያውሉ ሊታገዙ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ይህ አዲስ የመገናኛ ብዙሃን መሣሪያ ለተገባ ዓላማ ይውል ዘንድ ካህናት ቀርበው መሣሪያውን በማወቅ ወጣቱን ካደጋ የማዳን ኃላፊነት አለባቸው በማለት ከቫቲካን ረድዮ ጋር ያካሄዱት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.