2010-01-04 16:02:05

እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሥነ ሕይወት ኅብረ ዘር ዓመት


እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም. በምንኖርባት ምድር የሚገኙት የተለያዩ ሕይወት ያላቸውን የዘር ሃብት ጥበቃ ባህል በሚገባ እንዲረጋገጥ እና 34 ሺሕ የሚገመቱት የተለያዩ የዘር ሃብት ከምድረገ ገጽ ጨርሰው ይጠፋሉ RealAudioMP3 ተብሎ ከወዲሁ ግምት የተሰጠባቸው የተፈጥረ ዘረ ሃብት እግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህን ከመጥፋት አደጋ ለመከላከል እና በዚህ በምንኖርበት ዓለም ሕይወት ያላቸው የተለያዩትን የዘር ሃብቶች ለማክበር ቅስቀሳ የሚካሄድበት ዓመት ይሆን ዘንድ የተባበሩት መንግሥታት ያስተላለፈው ውሳኔ በማስመልከት፣ ግሪን ፒስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የዘር እና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ማኅበር በኢጣሊያ ተጠሪ አሌሳንድሮ ጃኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የስነ ሕይወት ዘረ ብዙ ሃብት አቅቦ እና አክብሮ የመኖሩ ሂደት የሁሉም ኃላፊነት ነው። የሰው ልጅ የሚከተለው የልማት እቅድ በተፈጥሮ የአካባቢ አየር ንብረት ላይ እያስከተለው ያለው ብከላ፣ የተፈጥሮ ያየር ንብረት መዛባት የመሳሰሉት አደጋዎች በስነ ሕይወት ሃብት አቢይ ጉዳት እያስከተለ እና አንዳንድ የዘረ ዓይነት ጨርሶ ለጥፋት አደጋ አጋልጦ እንደሚገኝ አስታውሰው፣ የምድር የሙቀት ደረጃ ከፍ እያለ በእንዲህ ከቀጠለ፣ በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ከሚገኘው የሥነ ሕይወት ዘረ ሃብቶች ውስጥ ከ 30 እስከ 40 በመቶ እንዲሚጠፉ አብራርተው፣ የስነ ሕይወት ዘረ ሃብት ለጥፋት እንዳይጋለጡ የሚያግዙ እቅዶች በሁሉም አገሮች ይነቃቃ ዘንድ አደራ ብለዋል።

የኢጣሊያ የግብርና ማኅበር ተጠሪ ጁዜፐ ፖሊቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የእስንሳሳት እና የአረንጓዴ ሃብት ጥበቃ እጅግ ማነቃቃት ያስፈልጋል፣ ይህ እቅድ በአለማችን የሚታየው የምግብ እጥረት እና እርሃብ ለማስወገድ ለሚደረገው ጥረት መሠረት ነው ካሉ በኋላ፣ ሥነ እርሻ የእያንዳንዱ አገር የአየር ንብረት የግብርናው ባህል ጭምር የሚያከብር መሆን አለበት፣ ተፈጥሮአዊው የፍጥረት ሂደት ለመጠበቅ የሥነ ሕይወት ዘረ ሃብት ጥበቃ እግብር ላይ ማዋል እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.