2010-01-04 16:02:17

ሰላም ለግብረ ሽበራ ተገቢ ምላሽ ነው


ከአምስተርዳም ወደ ተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ከተማ ደትሮይት ትበር በነበረቸው የሕዝብ አይሮፕላን በመጠቀም ግብረ ሽበራ ለመፈጸም አሸባሪያን የወጠኑት ሴራ መክሸፉ የሚዘከር ነው። RealAudioMP3 ይኽ ተጠንስሶ የነበረው የአሸባሪያን የጥቃት ሴራ ተጠያቂ በየመን ያደባው የአልቃይዳ የቀኝ እጅ የሆነው የአሸባሪያን ኃይል መሆኑ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ በይፋ በማሳወቅ፣ በዚህች አገር የሚገኘው የአመሪካ ልዑከ መንግሥት ጽ/ቤት እንዲዘጋ መወሰናቸው ተገልጠዋል። ለርእሰ ብሔር ኦባማ የጸረ አሸበሪያን ጉዳይ አማካሪ ጆን ብረናን አልቃይዳ በየመን ርእሰ ከተማ ሰንአ የሸበራ ጥቃት ለመጣል እቅድ እንዳለው ገልጠዋል።

የታላቅዋ ብሪታይን መራሄ መንግሥት ጎርዶን ብራውን አገራቸው እና የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት በጋራ አልቃይዳ ለሚዘነዝረው የሸበራ ጥቃት እና ሴራ ከወዲሁ ለማክሸፍ በየመን እና በሶማሊያ ያበረ የጸረ አሸባሪያን እቅዳቸውን እንደሚያሳይሉ አስታውቀዋል።

በበርይሩት የቅዱስ ዮሴፍ መንበረ ጥበብ የስነ አረብ ባህል ታሪክ እና የስነ ምስልምና ጥናት መምህር የእየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ሳሚር ክሃሊል ሳሚር ጥላቻ እና አመጽ የሚያስፋፋው የአሸባሪያን ሴራ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ በስልክ ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ሲመልሱ፣ በአሁኑ ሰዓት የሚታየው የአሸባሪያን እንቅስቃሴ እና ዛቻ አሸባሪያን ተስፋ እንደቆረጡ የሚያስገነዝብ፣ የሚያረጋገጥ ነው ካሉ በኋላ፣ አሸባሪያን በሰዎች ላይ ጭፍን የክፋት መንፈስ የተሞላው፣ ጉዳት እያስከተሉ ቢሆንም ቅሉ በሌላው ረገድ ሌሎችን ለመሳብ እና በእነርሱ ዓላማ ለማሳተፍ እና የሚያካሂዱት የፕሮፓጋንዳ እንቅስቃሴ በየትም አገር እንዲሁም በምስልምና እምነት ተከታዮች ጭምር ውጤት አልባ እየሆነ በመምጣቱ ምክንያት ተደናርበው ተስፋ ቆርጠው

የተለያዩ ጥቃት ቢሰነዝሩም፣ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ቢያስከትሉም ቅሉ ሌሎችን ለማሳመን እና የአገሮች መዋቅር እንደ አሸባሪያኑ ፍላጎት ለማዋቀር ያለመው የአልቃይዳው ዓላማ ብናኝ ሆኖ ቀርተዋል። ይህ ደግሞ ቅዱስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አመጽ የትም አያደርስም የሚያስገኘውም ውጤትም የለም ያሉትን ቃል የሚያረጋግጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በየመን እና በሶማሊያ ላይ ያነጣጠረ የጸረ አሸባሪያን ጥቃት በተመለከተ ብዙ እየተባለ ነው፣ ሆኖም አመጽ አመጽን እንጂ ሰላምን አያስገኝም፣ ምክንያቱን በሚሰነዘረው የጸረ አሸባሪያን ጥቃት ለአሸባሪያን ድጋፍ የሚሰጡ ወጣቶችን ማነቃቃት ነው የሚሆነው፣ ስለዚህ ይላሉ፣ ኢጣሊያ ለአገር ውስጥ አሸባሪያን የሰጠችው የጸረ አሸባሪያን ምላሽ እንደ አብነት በመጥቀስ፣ እነዚህ የአገር ውስጥ አሸባሪያን በሰው ሕይወት አቢይ ጉዳይ ያስከተሉ ቢሆንም ቅሉ የኢጣሊያው መንግሥት ሕግ ተገን በማድረግ እና በሰላም መሣሪያ አማካኝነት ተገቢ እና ሥር ነቀላዊ ምላሽ ለመስጠት ችለዋል። ስለዚህ አመጽን በአመጽ ግብረ መልስ መስጠት አመጽን መልሶ ማስፋፋት እና ማነቃቃት እንጂ አመጽን ጨርሶ ለማጥፋት አያግዝም፣ ሥር ነቀላዊው መልስ ሕግ መጠቀም እና ሰላምን ማነቃቃት ነው በማለት የሰጡትን ምላሽ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.