2009-12-31 17:03:36

የር.ሊ.ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ የተለመደውን አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት አሳርገው ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 96 ከቍ.7-13 “7 የአሕዛብ ወገኖች፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ 8 ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባን ያዙ ወደ አደባባዮችም ግቡ። 9 በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ። 10 በአሕዛብ መካከል። እግዚአብሔር ነገሠ በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል። 11 ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤ ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ፤ 12 በረሃ በእርስዋም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ፤ የዱር ዛፎች ሁሉ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል፤ 13 ይመጣልና፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በኤውሮጳ ዋና ዋና ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምረዋል።
“ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ በዚሁ የዚህ ዓመት የመጨረሻው የትምህርተ ክርስቶስ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ስለነበረው ስለ ትልቁ የንባበ መለኮት ሊቅ አቡነ ጴጥሮስ ሎምባርዶ መናገር እወዳለሁ። “ሰንተንሰ” የተሰኘው ድርሳናቸው ሰፊ ታዋቂነት እንዲኖራቸው አድርገዋል፣ ይህ መጽሓፍ እንደ የቤተ ክርስትያን ግብረ ገብነት ወይም ሞራላዊ ትምህርት ማስተማርያ ሆኖ ለረጂም ዘመናት አገልግለዋል። ይህ አቡነ ጴጥሮስ ሎምባርዶ ማን ነበር፦ያልን እንደሆነ፣ ስለ ሕይወቱ ታሪክ ብዙም ኣልተጻፈም ሆኖም ግን ከጽሑፎቹና ከሊሎች ጸሓፊዎች የሕይወቱ ታሪክ መሠረታዊ ነጥቦችን መልቀም እንችላለን። ብ11ና በ12ኛ ክፍለ ዘመን መሀከል ኖቫራ በሚባለው የሰሜን ኢጣልያ ክፍል አከባቢ ተወለዱ፣ መሬቱ የሎምባርዶ የሚባሉ መሀከለኛ ኑሮ የነበራቸው ቤተ ሰቦች ንብረት ስለነበር ከአቡነ ጴጥሮስ ስም ጋር ሎምባርዶ የሚቀለው ቅጽል እንገኛለን።

ለታሪኩ መሠረት ከሚሆኑን ቅዱስ በርናርዶስ ዘኪያራቫለ በፓሪስ የቅዱስ ቪቶርዮ ገዳም አበምኔት ለነበሩት ጀልድዊኖ በፓሪስ ለመማር ጉጉት ለነበረው ምጣኔ ሃብታዊ ዐቅም ግን ላልነበረው ወጣት ጴጥሮስ በገዳሙ ተቀብለው በነጻ እንዲያስቀምጡት አደራ ብለው ከጻፉት ደብዳቤ ነው።

በመሀከለኛው ክፍለዘመን በቤተክርስትያን ከፍተኛ ተቅዋማት ይማሩ የነበሩ፣ የመሳፍትና የመኳንንት ልጆች ብቻ ኣልነበሩም፣ ድኆችና ረዳት የሌላቸውም ይማሩ ነበር፣ እንደ ር.ሊ.ጳ. ጎርጎርዮስ 7ኛ ወይም ሄንሪ 4ኛን በመጠየቅ ትልቁን የኖትረ ዳም ዩኒቨርሲ ያነፁ የፓሪስ ሊቀጳጳስ የነበሩ ማውሪስዮ ዲዙሊ የድኆች ልጆች ነበሩ።

አቡነ ጴጥሮስ ትምህርታቸውን በበሎኛ ጀምረው ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ፓሪስ ሄዱ። ከ1040 ዓ.ም. በገናናው ትልቁ የኖትረ ዳም ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ሆኑ፣ ያኔ በ8ዓመታት የንባበ መለኮት ትምህርት ኣስተማሪነት ትልቅ አድራቆትና አክብሮት አትርፈዋል። በዘመኑ ጁልበርት ፓረታኖ የተባሉ ሊቅ ለየት ያለ ትምህርት ስላስተማሩና ትምህርታቸው ሊመረመር በተወሰነ ጊዜ ር.ሊ.ጳ ኤውጀንዮ 3ኛ የምርመራ ኃላፊነቱን ለአቡነ ጴጥሮስ ሎምባርዶ ሰጡት። ከክህነት በኋላ የፓሪስ ጳጳስ ሆነ እስከ ዕለተ ሞታቸው አገልግለዋል፣ ብ1060 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በዘመኑ እንደነበሩ የንባበ መለኮት ሊቃውንት አቡነ ጴጥሮስ ሎምባርዶም የተለያዩ ትምህርቶች መጻሕፍትና ድርሳናት ጽፈዋል፣ ትልቁ ድርሳናቸው በአራት መዝገቦች ወይም ቮልዩም የተከፋፈለ የቤተ ክርስትያንን ሞራል/ግብረገብ ትምህርት የሚመለከት “ሰንተንሰ” የተሰየመው ነው። ይህን መጽሓፍ በትምህርት እያስተማሩ ነው የጀመሩት እዛም ፈጸሙት ነው። ይህንን ለማድረግ በዘመኑ የቤተ ክርስትያን አበው ትምህርትና ሃሳብ ማጥናት ማወቅና አስተያየት መስጠት ይገባ ነበር፣ ከዚህም ጭምር የሌሎች ታማኝ ጸሓፊዎች ሃሳብን ማጥናት የግድ ነበር።

የመጽሓፉ መሠረት እንደ ቅዱስ አጎስቲኖስ የመሰሉት ትላልቅ የምዕራብ ቤተ ክርስትያን አባቶች፣ በጊዜው ከነበሩ ትላልቅ የንባበ መለኮት ሊቃውንት ክፍት በሆነ መንገድ በመራመር የቀረበ ነበር። እንዲሁም የግሪክ አበው ንባበ መለኮት ትምህርት ሰፊ መዝገብና፣ ከጥቂት ጊዝያት በፊት በምዕራባዊት ቤተ ክርስትያን የታወቀው በቅዱስ ዳማሸን የተደረስ የኦርቶዶክስ ሰፊ ትምህርትም ተጠቅመዋል።

የአቡነ ጴጥሮስ ሎምባርዶ ትልቁ አስተዋጽኦ ይህን በጥልቀት ያጠኑትናን ከልዩ ልዩ የአበው ትምህርት ያካበቱትን ትምህርት ሥርዓት አውጥተው በቅደም ተከተል ማቅረባቸው ነው፣ በንባበ መለኮት ጠባዮች ኣንድነትን በጠበቀ መንገድ መዝገበ ሃይማኖትን ማቀናበርና ማቀናጀት የግድ ነው። ሰንተንሰ በተባለው መጽሐፋቸው የተለያዩ ትምህርቶችን በአራት መዝገቦች አስፋፉ። የመጀመርያ መጽሓፍ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ያስተምራል፣ ሁለተኛ ስለ ፍጥረት ስለ ኃጢአትና ስለ የእግዚአብሔር ጸጋ ይናገራል፣ ሦስተኛ ስለ ምሥጢረ ሥጋዌና ስለ ምሥጢረ ድኅነት ሲሆን፤ አራተኛው ስለ ቤተ ክርስትያን ምሥጢራትና ስለ የሰው ልጅ ፍጻሜዎች በተለይም ስለ ዘለዓለማዊ ሕይወት ያስተምራል።

ይህ መጽሐፍ ሁሉን የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መዝገበ ሃይማኖት እውነቶችን ያካተተ ነው። መጽሐፉ ትልቅ አድናቆት እንዲያተርፍ ያደረጉት ጠባያት፣ አጠር ባለ መንገድ የቀረበ ንፁሕ የተስተካከለ በቅደም ተከተል በሥርዓትና በደንብ የተቀናበረ በመሆኑ ነው። በዚህም ተማሪዎች ቀለል ባለ መንገድ ይረዱት ነበር። አስታማሪዎችም ዕውቀታቸንና ምርምራቸውን በጥልቀት ለማከናወን ይረዳቸው ነበር። የአለስ አለሳንድሮ የተባለ ፍራንቸስካዊ የንባበ መለኮት ሊቅ ከአቡነ ጴጥሮስ በኋላ መጽሐፉን በጥናት በሚመች መንገድ አዲስ መግቢያና ክፍፍል ጨመረለት። ሌሎችም የአሥራ ስድስተኛ ክፍለ ዘመን ትላልቅ የንባበ መለኮት ሊቃውንት፣ እንደ ትልቁ አልበርት ቦናቨንቱራ ዘባኞረጆ የአኵኖ ቶማስ የትምህርት ጥናቶቻቸውን ሥራቸውን ይህንን መጽሐፍ በማጥናትና አስተያየት በማቅረብ ነው የጀመሩት። ይህ መጽሐፍ እስከ አሥራ ስድስተኛ ክፍለ ዘመን የንባበ መለኮት ትምህርት ቤቶች ይጠቀሙት ነበር።

በዚሁ አቀራረብ የክርስቶስ ምሥጢርን ማእከል ያደረገው የቤተ ክርስትያን ትምህርት እውነት፣ ሥርዓት ባለውና በተስትተካከለ መንገድ አንድ ሆኖ ይቀርባል። የአቡነ ጴጥሮስ ሎምባርዶ አብነትን በመከተል ሁሉንም የንባበ መለኮት ሊቃውንትና ካህናት በዘመናችን ካሉ የመለያየትና የመከፋፈል አደጋዎች ለመዳን የቤት ክርስትያን መዝገበ ሃይማኖትን ባጠቃላይ በአንድነት በመረዳት ለማስተማር እንዲችሉ አደራ እላለሁ። አዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መዝገበ ሃይማኖት በእምነትና በምስጋና መቀበል ያለብንን ይህንን ሙላት ያለው የክርስትያን የግልጸት ሥዕልን ያቀርቡልናል። ማኅበረ ክርስትያንና እያንዳንዱ ክርስትያን ግለሰብን፣ እነዚህን ፍሬዎች የእምነታችን ይዘት ለማወቅና በጥልቀት ለመረዳት እንዲጠቀሙዋቸው ለማበረታታት እወዳለሁ። እንዲህ ያደረግን እንደሆነ መዝገበ ሃይማኖቱ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ፍቅሩ ቀልባችን የሚስብና ተግባራዊ የፍቅር ምልሳችን የሚጠይቅ አስደናቂ ቅንብር ሆኖ ይቀርብልናል።

የአቡነ ጴጥሮስ “የሰንተንሰ” መጽሐፍ ምንኛ ያህል ብቃት እንዳለው ለመረዳት ቅ.አጎስጢኖስ በኦሪት ዘፍጥረት ያቀረበን ድርሳን በማጥናት፣ “እግዚአብሔር ሔዋንን ሲፈጥር ለምንድር ነው አጥንቱን ከአባታችን አዳም ጎን የወሰደው፣ ለም ከራስ ወይም ከእግር አልወሰደም፣ ብሎ ይጠይቃል። እንዲሁም ብሎ መልስ ይሰጣል፦ ለአዳም የተሰጠችው ሔዋን ገዢው ወይም ደግሞ አገልጋዩ ሳትሆን ከእርሱ ጋር እኩል የሆነች ጓደኛ ናት፣ ይህንን አምሳል ቤተክርስትያንና በክርስቶስ በማስመልከት፣ “አዳም እየተኛ እግዚአብሔር ከጎን አጥንቱ ሔዋንን እንድፈጠራት ሁሉ ቤተክርትያንንም ክርስቶስ በመስቀል ተስቅሎ እየተኛ ከጎኑ በፈሰሰው ደምና፣ ከቅጣት ያዳኑንና ከኃጢአት ነፃ ካወጡን ቅዱሳት ምሥጢራት ተወለደች” ይላል። እነኚህ አስተንትኖዎች ዛሬም ጥልቅና ለአስተንትኖ የሚሆኑ ናቸው። ንባበ መለኮትና ክርስትያናዊ ምሥጢረ ተክሊል የክርስቶስና የቤተክርስትያን ግኑኝነት እንደ ሙሽራና ሙሽሪት በአምሳል ለማቅረብ የረዳቸውም ይህ ጥልቅ አስተንትኖ ነበር።

በሌላም ቦታ ስለ የክርስቶስ ጸጋና መልካም ተግባር ሲናገር፣ የክርስቶስ መልካም ተግባር ለድኅነቱ በቂ ሊሆን ሲችል ለምን ክርስቶስ እንዲሰቃይና እንዲሞት አስፈለገ ብሎ ይጠይቃል። ሲመልስም “ለአንተ ነው! ለገዛ ራሱ አይደለም የሞተው” ይላል፣ በመቀጠልም “እንዴት ነው ለእኔ የሳቀየውና የሞተው” የሚለውን ጥያቄ ያስተንተንን እንድሆነ “ሕማማቱና ሞቱ ለአንተ አብነትና የድኅነት ምክንያት እንዲሆኑ ነው፣ የምግባረ ሠናይ ኃይልና የትህትና አበነት እንዲሆንህ የክብርና የነጻነት ምክንያት እንዲሆን ነው፣ ይህም እስከ ሞት ከታዘዘ እግዚአብሔር የተሰጠ አብነት የነፃነትህና የብፅዕናህ ምክንያት ነው።” ይላል።

ሌላው አቡነ ጴጥሮስ ሎምባርዶ ለቤተክርስትያን ካደርግዋቸው አስተዋጾኦዎች ስለ ቤተክርስትያን የሰጡትን ወሳኝ መግለጫ ለማስታወስ እወዳለሁ፣ ምሥጢረ ቤተ ክርስትያን ማለት የእግዚአብሔር ጸጋ ምልክት ሆኖ የማይታየውን ጸጋ በሚታይ ቅርጽ ይገልጻል፣ በዚህም የእግዚአብሔር አምሳልን በመግለጥ የዚሁ ምክንያት መሆኑን ይገልጻል። ይህንን መግለጫ ለማስፋት አቡነ ጴጥሮስ፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስትያን የጸጋ ምክንያኣት በመሆናቸው በእውነትም መለኮታዊ ሕይወትን ለመስጠት እንደሚችሉ ያብራራል፣ እርሱን የተከተሉ ሊቃውንት እስከአሁን ይህን ትምህርት ጠብቀውታል። የምሥጢራት ቍሳዊና ቅርጻዊ (ማተርያል / ፎርማል) ክፍሎችን የለያየ እርሱ ነው፣ ቍሳዊ የሚባለለው የሚታይ የሚጨበጥ ነገር ሲሆን ቅርጹ ደግሞ በካህኑ የሚደገመው ጽሎት ወይም ቃላት ናቸው። ብቃት ያለውና ፍጹም ምሥጢር ለማድረግ ሁለቱም መሠረታዊ አስፈላጊነት አላቸው። እግዚአብሔር እኛ የሚነካበት ቍሳዊ ነገር ሲሆን ትርጉም የሚሰጠው ደግሞ ቃሉ ወይም ቅርጽ ያልነው ነው። ይህንን ለመረትዳት የምሥጢረ ጥምቀት አፈጻጸምን የተመለከትን እንደሆን በሚጠመቅ ሰው ራስ ላይ የሚፈሰው ውኃ ቍሳዊ ነገር ሲሆን፣ ቅርጹ ደግሞ በአጥማቂው የሚደገም “እኔ በአብ በወልድና መንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቅሃለሁ” የሚሉ ቃላት ናቸው።

አቡነ ጴጥሮስ ሎምቫርዲ በእውነት የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚሰጡ ምሥጢራት ናቸው፣ ቍጥራቸውም ሰባት ናቸው፣ እነርሱም ጥምቀት ሜሮን ቅዱስ ቍርባን ንስሐ ምሥጢረ ቀንዲል ክህነትና ምሥጢረ ተክሊል ናቸው ይላል።

እግዚአብሔር በእነዚህ የቤተክርስትያን ምሥጢራት በመሀከላችን እውን ይሆናል፣ ይነካናል፣ ይለውጠናልም። አዲሱ የካቶሊክ ቤተክርስትያን መዝገበ ሃይማኖት እንደሚያስተምረው፦ “ምሥጢራት ምን ጊዜም ሕያውና ሕይወት ሰጪ ከሆነው ከክርስቶስ አካል የሚወጡ ኃይላት ናቸው። አካሉ በሆነችው ቤተ ክርስትያን የመንፈስቅዱስ ሥራ የሚገለጥባቸው ሥራዎች ናቸው። በአዲሱና በዘለዓለማዊው ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራዎች ናቸው።” ይላል።

በዚሁ በምናከብረው የካህ ዓመት ካህናትን በሙሉ በተለይም በነፍሳት እረኝነት ተሰማርተው ላሉት ካህናት፤ ምሥጢራትን ለምእመናን ለማደል የሚረዳቸው መጀመርያ ራሳቸው በምሥጢራቱ የሚመራ ሕይወት እንዲኖራቸው፣ በግላቸውም ይሁን ከማኅበረ ክርስትያን ጋር አብረው እንዲጸልዩ አደራ እላለሁ። ምሥጢራት ትልቁ የቤተ ክርስትያን መዝገብ ናቸው፣ እያንዳንዳችን በመንፈሳውነት እንድናሳርጋቸው ይጠየቃል። ተጨባጭ በሆኑ የምሥጢራት ምልክቶች ክርስቶስ አስደናቂ በሆነ መንገድ ሕይወታችን ይነካል፣ በእነርሱ አማካኝነት ሊያገነን ይመጣል፣ ያነጸናል፣ ይለውጠናል በመጨረሻም የመለኮታዊ ጓደኛነቱ ተሳታፊዎች እንድንሆን ብቃት ይሰጠናል።

የተከበራችሁ ጓደኞቼ፣ ይህንን ዓመት ጨርሰን በአዲስ ዓመት መባቻ እንገኛለን፣ በእያንዳንዱ የዚህ አዲስ ዓመት ቀን የክርስቶስ ጓደኛነት ይከተላችሁ ዘንድ የላቀ ምኞቴን እገልጻለሁ፣ ይህ ጓደኛነት ለእያንዳንዳችን ብርሃንና መሪ በመሆን የእርሱ ሰላም ሰዎች እንድንሆን ያብቃን፣ መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችው።” ሲሉ አስተምረው፣ ትምህርታቸውን ለመስማት ለተሰበሰቡት ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች አመስገነው ሓዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.