2009-12-27 18:44:28

በእውነት ጎዳና መመላለስ


ቅዱስ ኣባታችን በኩርያ ሮማያ ለሚታወቀው የቅድስት መንበር ድርገት ያደርጉትን ንግግር አስመልክቶ የቫቲካን ረድዮ ባልደረባ አለሳንድሮ ጂሶቲ የኪየቲ ቫስቲ ሊቀጳጳስና የንባበ መለኮት ሊቅ ለሆኑት ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ ኣስተያየት እንዲሰጡ ጠይቆአቸው ሲመልሱ “ባጭሩ ቅዱስነታቸው በእውነት ጎዳና እንድንመላለስ ነው ጥሪ ያቀረቡት፣ ይህንን ለማድረግ የመጀመርያው እርምጃ እያንዳንዳችን እግዚአብሔር በገለጸልን እውነት በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች ፊት በደላችን ማመን ለተገቢ ሰብአውነትና ለነጻነት አስፈላጊ ነው። እዚህ ላይ ቅዱስነታቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በትልቁ የሚለንዩም ኢዮቤል ‘የቤተ ክርስትያን ልጆች ለፈጸሙዋቸው ጥፋቶች ይቅሬታ እንጠይቃለን’ ያሉትን ይደግማሉ፣ ያኛው የይቅርታ ጥያቄ ያኔ የዓለም አቀፍ ንባበ መለኮታዊ ኮሚሽን ሊቀ መንበር በነበሩበት ጊዜ በኮሚሽኑ በታተመው ‘ዝክረ ኃጢአትና ዕርቅ’ በሚለው ጽሑፍ መሠረት ነበር፣ በጽሑፉ ‘እውነት ነጻ ያወጣችኋል’ በማለት እንደግለሰቦችና እንደቤተ ክርስትያን በእግዚአብሔርና በሌሎች ፊት እውነተኞች መሆን እንደሚያስፈልግ፣ ይህም እውነት ሰዎች እንደምሆናችን መጠን ድካማችንና በደላችንን ብናውቅም ቅሉ በጌታ ፊት እውነተኞችና የእርሱ ተከታዮች እንድንሆን ይረዳናል። ሲሉ አጠቃላይ አስተያየት ከሰጡ በኋላ የሚከተለው ጥያቄ ቀረበላቸው፣ በደልህን ማወቅ ፍጹም አለመሆንህን ማወቅ ሌላውን ሲቆጭ ለክርስትያን ግን የእውነተኛ ሰብአውነት ምልክት ሲባል ምን ማለት ነው፦ ብፁዕነታቸው ሲመልሱ ‘ለመሆኑ ይህ በጌታ ኢየሱስ ትምህርት የነጻነታችን ምልክት ነው፣ እውነት ነጻ ያወጣችኋል ማለት እኮ ከማንኛውም ማስመሰል ነጻ በሆነ መንገድና እውነትን በመመርኮስ ፍጹም አለመሆንን ማወቅ በእግዚአብሔርና በኅልናችን ፊት እንዲሁም በሌሎች ፊት እውነተኛ ማንነታችን መግለጥ ነጻነት ነው፣ ነጻነት ደግሞ ክቡር የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ይህ ነጻነት ሕይወትን በሙላት እንድንኖር የእውነትና የደስታ ሕይወት ያደርጋታል። ለዚህም ነው ቅዱስነታቸው የኢየሱስ ትምህርት በመከተል በደላችን ማወቅ የነጻነትና የእውነት ጉዞ መነሻ መሆኑን የገለጹት።’ ብልዋል።

የቅዱስነታቸው ጥሪ ምሥጢረ ዕርቅ የሆነው ምሥጢረ ንስሐን እንደገና ለማስተማር እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ የዚህ ምሥጢር አስቸኳይ አስፈላጊነት ቅዱስነታቸው እንደገለጹት ‘በእውነት ጎዳና ማለትም በነጻነት ጎዳና መመላለስ ካለ ብቻ ነው እውነተና ዕርቅ የሚገኘው፣ የእግዚአብሔር ምሕረት ጽድቅና ነጻ የሚያወጣን እውነት ስንቱን እንደሚያስፈልገን ልንገነዘብ የምንችለውም በዚህ ነው፣ ይህንን ሁሉ የምናገኝበት ቦታም በምሥጢረ ንስሐ ነው። ብለው ካብራሩ በኋላ በመጨረሻ ቅዱስነታቸው ሩቅ ካሉ ጋርም እንድንወያይ እምነት ከሌላቸውም ሳይቀር ግንኙነት እንድንመሥርት የሚጠይቁ ይመስላል፣ አስተያየትዎ እዚህ ምን ነው ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፤ እንደ እውነቱ ከሆነ በእውነት ጎዳና ሲመላለስ አምናለሁ የሚል ሰው እምነቱ ምን ያህል ትንሽ እንደሆነ ኣንዳንዴም ኣለማመኑን ስለሚያረጋግጥ በየዕለቱ ለማመን መጀመር እንዳለበት ይረዳል፣ በሌላ በኩል የሆነ አረሜን ከእውነት ለመሸሽ ካልፈልገ ‘እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ’ ሳይሆን ‘እግዚአብሔር ቢኖር ኖሮ’ ብሎ ነው የሚያስበው፣ በዚሁ የእውነትና የነጻነት ድንበር አማንያንና ኢኣማንያን የሚያገናኛቸው ቦታ ኣላቸው። ይህም ለመወያየት አንዱ ሌላውን በማክበር የእውነት ብርሃን ልባቸውን እንዲያበራ መዘጋጀት ያስፈልጋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.