2009-12-27 18:45:40

በእስፓኛ የተደነገገው ፅንስ የማስወረድ አዲስ ሕግ የግፍ መሆኑ ተገለጠ።


ባለፉት ቀናት የእስፓኛ የሕግ መምርያ ምክር ቤት ፅንስ ማስወረድን ነጻ ተግባር የሚያደርግ ሕግ ማፅደቁና ለውሳኔ ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ በረቁቁ ሕግ መሠረት ከፅንስ እስከ 14ኛ ሳምንት ማስወረድ እንደሚፈቅድ አዳጋች በሆኑ ሁኔታዎች ደግሞ እስከ 22ኛ ሳምንት ፅንስ ማስወረድን ይፈቅዳል።

የአልካላ ደ ሄናረስ ጳጳስና የእስፓኛ ጉባኤ ጳጳሳት የቤተ ሰብና የሕይወት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኽዋን አንቶንዮ ረይግ ፕላ ሕጉን የግፍ ሕግ ሲሉ አውግዘውታል። ለቫቲካን ረድዮ በስልክ በሰጡት አስተያየት፣ ‘ይህ ግን እውነትም የግፍ ሕግ ነው፣ የቀድሞ ሕገ መንግሥታችን ፅንሱ የሚያስከትለውን አድጋ እግምት ውስጥ በማስገባት ፅንስ ማስወረድን ይፈቅድ ነበር፣ አሁን ሴት ልጅ በማሕጸንዋ ያለውን ሕጻን ሕይወት ለማጥፍት መብት አላት ይላል፣ የንጹሓን ሕይወት ማጥፋትን እንደ መብት ሕገ መንግሥት ውስጥ የሚያኖር የመብት መንግሥት ሳይሆን አምባገነን ነው፣ ይህ ሕግ ሕይወትን ማጥፋትን እንደ መብት ብቻ ኣይደለም የሚያኖረው ይህንን ጨካኝ ፍጻሜ ሲፈጸም ላለመርዳት ኅሊናቸው የማይፈቅድላቸው የሕክምና ሠራተኞችንም ኅልናቸውን የሚጻረር ተግባር እንዲፈጽሙ ስለሚያስገድድ ይህ ደሞክራሲ ኣይደለም፣ የኅሊናን ነጻነትና መብት መጠበቅ የጤነኛ ደሞክራሲ ምልክት ነው፣ ይህ የሕክምናን ዓላማ ያዋክባል፣ የሕክምና ዓላማ ሕይወትን መዳን እንጂ ሕይወትን ማጥፋት ኣይደለም፣ እንደሚመስለኝ ይህ የሞት ባህል ምልክት ነው፣ ሲሉ ምረታቸውን ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.