2009-12-18 14:30:01

የክርስትያን እና የአሁድ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት ቀን


በኢጣሊያ የካቶሊክ እና የአይሁድ ሃይማኖቶች የጋራ የወይይት ቀን እ.ኤ.አ. ጥር 17 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚከናወን ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ። ይህ በካቶሊክ ቤተ ርክስያን እና በአይሁድ ሃይማኖት መካከል RealAudioMP3 የሚደረገው የወይይት ቀን፣ የጋራ ውይይት ጥልቀ ሂደት እና እድገት በሚል ርእስ የተመራ እንደሚሆን የዜናው አገልጎት በማሳወቅ፣ ይኸንን ጉዳይ የሚያስረዳ አጭር ሰነድ በኢጣሊያ ለሚገኙት የካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን መሰራጨቱ ለማወቅ ተችለዋል።

ሰነዱ ዳብሊው ዳብሊው ዳብሊው ኪየዛካቶሊካ ነጥብ አይቲ በሚል ድረ ገጽ አማካኝነት መሰራጨቱም ሲገለጥ፣ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ከተለያዩ ሃይማኖት ጋር የሚደረገው ግኑኝነት የሚንከባከበው ድርገት ሊቀ መንበር የተርኒ እና አመሊያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪቸንዞ ፓሊያ እና የኢጣሊያ የአይሁድ አይማኖት መንፈሳውያን መሪዎች ጠቅላይ መሪ ራቢ ጁዜፐ ላራስ በጋራ የፈረሙበት ሰነድ ሲሆን፣ ይህ የጋራው ውሳኔ እ.ኤ.አ. መስከረ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢጣሊያ የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፅዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ እና የኢጣሊያ የአይሁድ አይማኖት መሪዎች ጠቅላይ ሊቀ መንበር ራቢ ጁዜፐ ላራስ መካከል በተካሄደው ግኑኝነት ቀድሞ የተወሰነ መሆኑ ሲር የዜና አገግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.