2009-12-18 14:23:45

የሰብአዊ ክብር ሰላም እና የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና በቅድስት መንበር የዴንማርክ የሱዳን የኡጋንዳ የኬኒያ የለቶኒያ የፊንላንድ የካዛኪስታን የባንግላደሽ ልኡካነ መንግሥት በመሆን ከመንግሥቶታቸው የተላኩት ያቀርቡት የሹመት ደብዳቤ በመቀበል RealAudioMP3 የሰብአዊ ክብር፣ ሰላም እና የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ማእከል ያደረገ ንግግር ማቅረባቸው ከቅድስት መንበር የተላለፈልን የዜና ምንጭ ያረጋገጣል።

ቅዱስነታቸው ሰላም ውይይት ማኅበራዊ ፍትህ በማህበራዊ እድገት የሃይማኖቶች ሚና ድኾች እና በጠና ድኽነት እና ስቃይ ላይ ለወደቁት ጥበቃ እና የሃይማኖት ነጻነት መከበር በሚሉት ርእሶች የያንዳንዱ ልኡካነ ብሔር የሹመት ደምዳቤ በመቀበል ባሰሙት ንግግር በማሳሰብ፣ የዴንማርክ ልኡከ መንሥት ሃንስ ክሊንገበርግ ያቀረብቱ የሹመት ደብዳቤ ቅዱስነታቸው በመቀበል በተባበሩት መንግሥታት አነሳሽነት በኮፐንሃገን በመካሄድ ላይ ያለው የተፈጥሮ ያካባቢ አየር ጥበቃ ርእሰ ማእከል ያድረገው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ በመጥቀስ አገሮች ብሔራዊው ፈቃዳቸውን እና ፍላጎታቸውን ለመላ ዓለም ጥቅም ላቀና ዓላማ ማረጋገጫ እንዲያውሉት በማሳሰብ መጪው ትውልድ የሚረከባት የምንኖርባት ዓለም በኃላፊነት እንክብካቤ የተደረገላት የሁሉም ፍጥረት መኖሪያ መሆኗ የተረጋገጠባት ትሆን ዘንድ አደራ ብለዋል።

ቀጥለውም የሱዳን ልኡከ መንግሥት ሱለይማን ሞሃመድ ያቀረቡትን የሹመት ደብዳቤ በመቀበል ቅዱስነታቸው ባሰሙት ንግግር ዳርፉርን በመጥቀስ፣ የዚህ ክልል ነዋሪው ሕዝብ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ እንደሚገኝ በማስታወስ፣ በክልሉ የጦርነት እና የግጭቶች ተወናያን የሆኑ ሁሉ በውይይት ጠረጴዛ ዙሪያ ተገናኝተው ውጥረቱን በውይይት ይፈቱት ዘንድ ጥሪ በማቅረብ፣ ግጭት በውይይት በፍትህ እና በእውነተኛው እርቅ ብቻ ነው የሚፈታው ብለዋል።

የኡጋንዳ ልኡከ መንግሥት ፍራንቺስ ቡታጂራ ለቅዱስነታቸው የሹመት ደብዳቤ ማቅረባቸውም ሲገለጥ፣ ቅዱስ አብታችን የሹመቱን ደብዳቤ ተቀብለው፣ በኡጋንዳ ሰሜናዊ ክልል የሚኖረው ሕዝብ የተጋረጠበት አሰቃቂው እና አሳዛኙ አመጽ፣ በዚሁ አመጽ ምክንያት ወላጅ አልባ ሆነው የቀሩትን ጋለሞታዎች እና ተፈናቃዮች በጠቅላላ ተገቢ ድጋፍ እና ትብብር እንዲደረግላቸው በማሳሰብ፣ የሕይወት ደህንነት እጦት የዘርፈ ብዙ ችግር ምንጭ ነው ካሉ በኋላ፣ በዚህች አገር የሰላም የሕይወት እና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ በሚመለከቱ ጉዳዮች ሕንጸት ይረጋገጥ ዘንድ አደራ ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በመቀጠል የኬንያ ልኡከ መንግሥት ኤልካናህ ኦደምቦ ያቀረቡትን የሹመት ደብዳቤ በመቀበል፣ በኬኒያ የዛሬ ሁለተ ዓመት የተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ምክንያት በዚህች አገር የተከሰተው አመጽ፣ ማኅበራዊ ውጥረት በማስታወስ ለዚህ ዓይነቱ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ችግር የሚዳርገው ሁሉ በውይይት ተወግዶ ሰላም እና መረጋጋት እንዲረጋገጥ አደራ ብለዋል።

በመቀጠልም የለቶኒያ ልኡከ መንግሥት ኤይናርስ ሰማኒስ ያቀረቡት የሹመት ደብዳቤ በመቀበል ቅዱስ ኣባታችን ባሰሙት ንግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኤኮኖሚው ቀውስ በዚህች አገር ያስከተለው ኤኮኖሚያዊ ችግር ያስፋፋው ድኽነት ሥራ አጥነት መጪው ሕይወት የሚያናጋ ሁኔታ እንዲከሰት ማድረጉ አስታውሰው፣ የአገሪቱ መንግሥት እነዚህ እክሎችን ለመቅረፍ በብርታት ይንቀሳቀስ ዘንድ አደራ በማለት አክለውም፣ ር.ሊ.ጳ. ኢኖቸንዞ ሶስተስኛ ለቶኒያ የማርያም መሬት የሚል የሰጡዋት ስያሜ በማስታወስ፣ የዚህች አገር ክርስትያናዊ መሠረት ያለው ባህልዋ በመጥቀስ፣ ይህ ባህል ይንጸባረቅ ዘንድ አደራ ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የፊንላንድ ልኡከ መንግሥት አልፖ ሩሲ ያቀረቡት የሹመት ደብዳቤ ተቀብለው፣ ፊንላንድ ለድኾች አገሮች የምትሰጠው ድጋፍ ለስደተኞች እና ለተፈናቃዮች የምታቀርበው ድጋፍ ልዩ የሚያደርጋት መሆኑ ዘክረው፣ አገሪቱን በማድነቅ ሆኖም ግን ተባባሪነት ድጋፍ አቅርቦት በሰብአዊ ክብር ዘንድ ያለው ሓቅ አይተካውም ብለዋል።

የካዛኪስታን ልኡከ መንግሥት ሙክህታር ቲለውበርዲ ያቀረቡት የሹመት ደብዳቤ ተረክበው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባሰሙት ንግግር በሃይማኖቶች መካከል ያለው ጉንኝነት እንዲጠናከር በማሳሰብ በዚህች አገር በእስላም እና ክርስትያን ሃይማኖት መካከል ከመከባበር እና ከመተዋወቅ የመነጨ መልካም ግኑኝነት እንዲረጋገጥ አደራ ብለዋል።

በቅድስት መንበር አዲስ የባንግላደሽ ልኡከ መንግሥት አንዱል ሃናን ለቅዱስ አባታችን የሹመት ደብዳቤ ማቅረባቸውም ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን በዚሁ አጋጣሚ ባሰሙት ንግግር፣ ይህችን አገር በጠና የሚያሰቃየው ድኽነት እና መሃይምነት ለማስወገድ ብሎም ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት በሕንጸት መርሃ ግብር የተሸኘ እንዲሆን አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.