2009-12-18 14:28:33

የሃይማኖት መገልጫ ምልክቶች


ባለፈው ወር በስትራስበርግ የሚገኘው የኤውሮጳ ኅብረት የሰብአዊ መብት አስከባሪው የበላይ ፍርድ ቤት፣ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች የእምነት መግለጫ የሆኑት ምልክቶች እንዳይሰቀሉ RealAudioMP3 ያስተላለፈው ውሳኔ፣ የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊወያይበት መሆኑ ሲገለጥ፣ ትላትና ይወያይበታል ተብሎ ሲጠበቅ በዚህ የኤውሮጳ ህብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሶሻሊስ እና ለዲሞክራሲ የግራ የፖሊቲካ ሰልፎች የሚወክሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሊቀ መንበር ማርቲን ሹልዝ ያቀረቡት ሐሳብ በመቀበል፣ ርእሰ ጉዳዩ ለሚቀጥለው የህብረቱ ይፋዊ ጉባኤ መሸጋገሩ ተገልጠዋል።

በኅብረቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀኝ የመሃል የፖለቲካ ሰልፎችን የሚወሉት የሚታቅፈው የኤውሮጳ ሕዝባዊ የፖለቲካ ሰልፍ የህብረቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ርእሰ ጉዳይ ለሌላ የውይይት ቀነ ቀጠሮ ከማሻገሩ ይልቅ አሁኑኑ ቢወያይበት እና ስለ ጉዳዩ አንድ ውሳኔ ቢያስተላልፍ የተሻለ ነበር በማለት አስተያየት ሰጥቷል።








All the contents on this site are copyrighted ©.