2009-12-18 14:27:23

ኮንጎ፣ ጸረ አቢያተ ክርስትያን ያቀና ጥቃት


በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ በሚገኘው ደቡባዊ ኩቩ የተጀመረው ጸረ ቤተ ክርስትያን ጥቃት አሁን እየቀጠለ መሆኑ ተገለጠ። ባለፈው እሁድ የጦር መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች በቡካቩ ክልል የሚገኘው RealAudioMP3 አንድ ገዳም ማጥቃታችው እና አንዲት ድንግል ለሞት መዳረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በደቡባዊ ኩቩ አማጽያን ኃይሎች የተያያዙት ጥቃት አሁንም በመቀጠል፣ መኖሪያ ቤቶች መንደሮች በእሳት በማጋየት ሰዎችን በመጥለፍ ሴቶችን በመድፈር እና ሞት በማስከተል በሰው እና በንብረት ላይ አቢይ ጉዳት እያስከተሉ ናቸው።

ባለፈው ማክሰኞ የቡካቩ እና የኡቪራ ክርስትያን ማኅበረሰብ አመጹን በመቃወም የሰላም ጠሪ የእግር ጉዞ መርሃ ግብር በጋራ ማካሄዳቸው ሲገለጥ፣ ተከስቶ ያለው አመጽ እና በቤተ ክርስትያን እና በአባሎቿ ዘንድ ከአመጽያን ኃይሎች እየደረሰ ካለው አደጋ ለመከላከል የቡካቩ ቤተ ክርስትይን ወሉደ ክህነት እና የደናግል ማህበራት በጋራ የደህንነት እና የጸጥታ ጉዳይ በተመለከተ ለአገሪቱ ርእሰ ብሔር ጆሴፍ ካቢላ መልእክት ማስተላለፋቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

የቡካቩ ሰበካ የፍትሕ እና የሰላም ድርገት ሊቀ መንበር አበምኒየት ጁስትን ንቡንጂ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የክልሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሰላም እንዲወርድ የሰላም ባህል ለማስፋፋት ለወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል የምትሰጠው የሰላም ሕንጸት የአመጽያን ኃይሎች እንቅስቃሴ የሚገታ እና እንዲወገድ የሚያደርግ በመሆኑ ይኸንን በመሥጋት ታጣቂ ኃይሎች በቤተ ክርስትያን እና በአባላቶቿ ላይ የሚሰነዝሩት ጥቃት መሆኑ ገልጠው፣ ይህ ጥቃት ቤተ ክርስትያን ከቆመችበት ዓላማ እይገታትም፣ ለሰላም ከመቆም እያግዳትም ካሉ በኋላ፣ የቤተ ርክስትያን ዓላማ የትጥቅ ትግል የሚቃወም በመሆኑ ምክንያት ቤተ ክርስትያን ለተለያዩ አደጋዎች አጋልጧት ይገኛል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.