2009-12-18 14:24:31

ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ


ቅዱስ ኣባታችን ትላትና ጧት በቫቲካን በሚገኘው በእመ መድኃኔ ዓለም ቤተ ጸሎት ለብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ 90 ዓመት እድሜ ምክንያት ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት፣ ባሰሙት ስብከት እኚህ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል RealAudioMP3 የቲዮሎጊያ ሊቅ እ.ኤ.አ. ታሓሳስ 17 ቀን 1919 ዓ.ም. በሞራቪያ በቀድሞ ቺኮዝላቫኪያ በአሁኑ ወቅት ሬፓብሊክ ቸክ በሚል ስም በምትጠራው አገር መወለዳቸው ዘክረው፣ እኚህ አቢይ የቲዮሎጊያ ሊቅ የድህነት ታሪክ በቅድስተ ሥላሴ ገጽታ እና ሓቅ በመተንተን እግዚአብሔር በአምሳያችን ሰው እንፍጠር ብሎ በአርአያው እና በአምሳያው ሰውን ሲፈጥር ይኽ ደግሞ የነጻነት እና የፍቅር አቢይ ሚስጢር መሆኑ ሰው በሙላት ከእግዚአብሒር ጋር ውህደት ሕብረት እንዲኖረው የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ፍቃድ የተሰጠ ጸጋ ነው። በሌላው አነጋገር ሰው እግዚአብሔር ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር እንዲሆን እግዚአብሔር ፍቅዶ በአርአያው እና በአምሳያው ፈጥሮታል፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ያለው ክብር ምንኛ የላቀ መሆኑ በጥልቀት በስነ ቲዮልጊያ በመተንተን ያብራሩ ናቸው ብለዋል።

እግዚአብሔር ሰው እንደ እግዚአብሔር እንዲሆን ፈጠረው ሲባል፣ በውስጡ እግዚአብሔራዊ ክብር አለው ማለት መሆኑ በማብራራት፣ ይህ የእግዚአብሔር ሦስትነቱን ሰውን በመፍጠር የተገለጸው እውነት በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የተረጋገጠው ውህደት በገዛ ራሱ የሚቀር ሳይሆን፣ የምሥራቁ ክርስትና እንደሚያስተምረው፣ መለኮታዊ ሰው እርስ በእርሱ የሚያፋቀር ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የሰው ልጅ በነጻነት እና በፍቅር የጸና መሆኑ የሚያረጋግጥል ነው፣ ይህ እውነት በምርምር የሚጨበጥ ሳይሆን በእውነተኛው እና ፍጹም እግዚአብሔር እና ፍጹም ሰው በሆነው በሚስጢረ ክርስቶስ እና ከርሱ ጋር በሚጸናው በኅላዌአችን ዘንድ ያለው ውህደት ስብእናዊ መለኮት አማካኝነት ብቻ ነው የምንገነዘበው ካሉ በኋላ ይኽ ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ ትምህርት ብፁዕ ካርዲናል ስፒድሊክ ተንትነውታል።

የዕለቱን ንባበ ወንጌል መሠረት የኢየሱስ የትልድ ዘር ሲያስረዱ፣ በዚህ የትውልድ ሃረግ አካብ ሩት ቤትሳበአ እና ታማራ የተባሉ አራት እምነት ካልተቀበሉ ዘር የሆኑት ሴቶች ስም እናገኛለን ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር የማዳን ሚስጢር ይኽንን ሚስጢር የምትሰብከው ቤተ ክርስትያን ጭምር ኵላዊነታቸውን የሚያመለክት ማለትም የማዳን ታሪክ ሁሉን የሚያጠቃልል መሆኑ የሚያስረዳ ነው ካሉ በኋላ የዛሬ 10 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይህ የእመ መድሃኒ ዓለም ቤተ ጸሎት ሲባርኩ፣ የዚህ እመ መድሃኒ ዓለም ታሪክ እና አምሳያ የእግዚአብሔር የፍቅር ሚስጢር፣ እኛን የእግዚአብሔር ልጆች የሚያደርገን ኃይል ሊሰጠን ሰው ሆኖ ወደ እኛ መምጣቱን የሚያረጋገጥልን ነው። ክርስቶስ ከማርያም በመወለድም ይህ የማዳን እና የደስታ መልእክት ለሰው ልጅ ተሰጠ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.