2009-12-16 18:21:07

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዓለም አቀፍ መልእክተ ሰላም ለ2010 ዓ.ም.


 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለሚቀጥለው ዓመት 2010 እኤአ የሚያስተላልፉት ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት ይፋ ሁነዋል።

የቅድስነታቸው የሰላም መልእክት ይፋ የሆነው በየቅድስት መንበር ማኅተም ክፍል ሲሆን ይፋ ያደረጉት በቅድስት መንበር የቀድሞ የፍትሕና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁዕ ካርዲናል ረናቶ ራፋኤለ ማርቲኖ እና የምክር ቤቱ ወቅታዊ ዋና ጽሐፊ ናቸው ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በቅርቡ ለሚከበረው አዲስ ዓመት 2010 ለመላ ዓለም የሚያስተላልፉት የሰለም መልእክት ርእስ ሰላም ለማልማት ወይም ለማግኘት ፍጥረትን ጠብቅ የተሰየመ እንደሆነ ይታወቃል።

መንግስታትም ሆኑ ግለ ሰዎች ሀብታሞችም ሆኑ ድሆች ፍጥረትን የመንከባከብ እና መጠበቅ ሐላፊነት እና ግዴታ እንዳላቸው የሚያመልከት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሰላም መልእክት ቤተክርስትያን ከአንድ መቶ ዓመት በፊ ጀምራ የአከባቢ ጥበቃ እና የዓለም ሰላም ትኩረት በመስጠት ፡ በርካታ ሰነዶች ለዓለም ህዝቦች ይፋ ማድረግዋ ያስታውሳል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለኦን አስራ ሶስተኛ ግንቦት አስራ አምስት ቀን 1898 እኤአ ሮሩም ኖቫሩም አዲስ ነገሮ የተሰየመ ማህበራዊ ሐዋርያዊ መልእክት ፡ ከሀያ ዓመታት በፊት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለፍጥረት ጥበቃ አስፈላጊውን እንክብካቤ ባለ መደረጉ የተነሳ የዓለም ሰላም አስጊ እየሆነ መምጣቱ ያስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት በየሰላም መልእክቱ ተወስተዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሰላም መልእክት በአሁኑ ወቅት አከባቢ በሚገባ ባለ መጠበቁ እና የአየር ጸባይ በመለዋወጡ ህዝቦች አከባቢያቸው ሲለቁ እንደሚታዩ ምድረ በዳዎች እየተስፋፉ ውቅያኖሶች እየተበከሉ ብዝሀ ሕይወቶችም እየጠፉ መሆናቸው ያሳስባል።

ዞሮ ዞሮ የሰው ልጅ የነዚህ ቀውሶች ሰለባ እየሆነ ስለሆነ ፍጥረትን መንከባከብ እና መጠበቅ የሁሉ ኃለፊነት መሆኑ ሰው ራሱን የሚጐዳ በገዛ ራሱ ከመፈጸም እንዲቆጠብ የሰላም መልእክቱ እንደሚጠይቅ ተስተውለዋል።

ለሰው ልጅ የሚገጥሙት የኤኮኖሚ ማኅበራዊ እና የአከባቢ ቀውሶች እርስ በእርስ የተሳሰሩ ሞራላዊ ቀውሶች መሆናቸው መዘንጋት እንደማይገባ የሰላም መልእክቱ ያመልከታል።

በእግዚአብሔር የተቸረ ፍትረት በግድ የለሽነት እና ራስ ወዳድነት ከማውደም መንከባከቡ እንደሚያሻ የፍጥረት ቅርሶች የሰው ሁሉ ውርሻ እና እሴቶች መሆናቸው መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑንም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት ያስገነዝባል።

የአከባቢ ጥበቃ በሚመለከት ከኤኮኖምያዊ ጥቅም ነፃ የሆነ የረጂም ግዜ ፕሮግራም ካልተቀየሰ የሚመጡ ትውልዶች ለኃይለኛ ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉም ነው መልእክቱ የሚያሳስበው።

ተፈጥሮአዊ ሀብቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዋሀደ አስተዳደር ለመቆርቀር በሳይንስ እና ተክኖሎጂ ጥናት የተመረኮሰ አስተዳዳር እንደሚያሻ የሰላም መልእክቱ በሐሳብ መልክ አቅርበዋል ።

የሰላም መልእክቱ በማያያዝ በአንድ ኅብረተሰብ ውስጥ ሰብአዊ ሥነ ሕይወት ማእከል ያደረገ እድገት ከተካሄደ ይህን ተከትሎ የአከባቢ ሥነ ሕይወትም የተጠበቀ ሊሆን እንደሚችል

ያመለከተ መልእክተ ሰላሙ ቤተክርስትያን ፍጥረት እና አከባቢ ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ የበኩልዋ እንደምትጋደርግም አመልክተዋል ።

!!!!!ይህ በዚህ እንዳለ የሰላም መልእክቱ ለመገናኛ ብዙኀን ያቀረቡት በቅድስት መንበር የቀድሞ የፍትሕና ሰላም ጳጳሳዊ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ረናቶ ራፋኤለ ማርቲኖ እንደገለጹት፡

መልእክተ ሰላሙ ፍጥረትን ለመታደግ መሠረታዊ የባህል እና የሥነ ምግባር ለውጥ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥቶ የሚጠቅይ መልእክት ነው ።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሥነ ሕይወት መልእክት የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እና ፍጡር ሁሉ ያላቸውን ሕይወታዊ ግንኙነት በመገንዘብ የሰው ልጅ ከራስ ውዳድነት እና ግድ የለሽነት ተላቆ የተሰጠውን አእምሮ በመጠቀም አከባቢውን እንዲጠብቅ የምያሳስብ መልእክት መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ረናቶ ራፋኤል ማርቲኖ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል በደንማርክ ርእሰ ከተማ ኮፐንሀገን ላይ የአየር ንብረት ትኩረት የሰጠ ጉባኤ እየተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ፡የዓለም መሪዎች ጉባኤ ስኬታም እንዲሆን ብፅዕነታቸው ያላቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል። የቫቲካን የልኡካን ቡድን በዚሁ የኮፐንሀገን ጉባኤ ተሳታፊ መሆኑ የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.