2009-12-16 17:43:31

የር.ሊ.ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ 15.12.2009


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ሮብ በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ ሰጡ። ጉባኤ አስተምህሮውን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ የሚከተለው ቃለ እግዚአብሔር ከ በተለያዩ ቋንቋዎች ተነበበ። ቅዱስነታቸው በጣልያንኛ ቋንቋ በስፋት ያቀረቡትን ትምህርት ጨምቀው በሌሎችም የኤውሮጳ ቋንቋዎች አቅርበዋል፣ ለዛሬ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያስተማሩትን እናቀርባለን። “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ ዘወትር በዚሁ የትምህርተ ክርስቶስ ክፍል እንድምናደርገው ዛሬም በጀመርነው የመሀከለኛ ክፍለ ዘመን የክርስትያን ትህምርት ባህል በመቀጠል በ12ኛው ክፍለ ዘመን ስለነበረው ዝነኛ የፍልስፍናና የትምህርተ መለኮት ሊቅ አቡነ ዮሐንስ ዘሳልስበርይ ትምህርት እንመለከታለን። አቡነ ዮሐንስ እንግሊዝ አገር የተወለዱ ሲሆን ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በፓሪስና በሻርትር ነበር። አቡነ ዮሐንስ የቅዱስ ቶማስ በከት ጓደኛና ተባባሪ ነበር። በቤተ ክርስትያንና በንጉሥ ሄንሪ ዳግማዊ በተነሣው ክርክርም ገብቶ ነበር። የሻርትር ጳጳስ ሳሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

መታሎጊኮን በተባለው ድርሳኑ ስለ ፍልስፍና “እውነተኛ ፍልስፍና በጠባዩ ለሁሉም የሚዳረስ ነው፣ እውነተኛ ፍልስፍና በጥበብ መልእክቱ ኅብረተሰብን በሐቅና በበጎነት ለመገንባት ያገልግላል” ሲል ያስተምራል። አቡነ ዮሐንስ የሰ ልጅ አእምሮ ውስንነትን ሳይክድ በመግባባትና በድርድር የሰው ልጅ አእምሮ እውነትን ለማወቅ ይችላል፣ የእግዚአብሔርን ፍጹም እውቀት ለመካፈል የሚረዳን እምነት የአእምሮን ችሎታ እውን ለማድረግ እንደሚረዳም አስተምሮዋል።

ፖሊክራቲኩስ በተባለው ሌላ ድርሳናቸው ደግሞ፣ የሰው ልጅ አእምሮ አድማሳዊ የተፈጥሮን ሕግ መሠረት በማድረግና በአዎንታዊ በኩሉ እሱን በመታዘዝ የተመዛዘነና ያልተዛባ እውነትን ማወቅ የሚያስችል ብቃት እንዳለው ያስተምራል።

የአቡነ ዮሐንስ ጥልቅ ትምህርት ለዘመናችን እጅግ ኣስፈላጊ ነው፣ የዘመናችን ሕገጋት በንጹሕና ትክክለኛ አእምሮ ሳይሆን እውነት ተዛማጅ ነው በሚለው አምባገነን የተደነገጉ ስለሆነ የአቡነ ዮሐንስን ትምህርት እንደገና በማጥናት የሐቅና የፍትሕ ዓላማዎች ምንጭ በሆነው የተፍጥሮ ሕግና ትክክለኛ የሰው ልጅ አእምሮን በመጠቀም እናሻሽላቸው።” በማለት ትምህርታቸውን ለመስማት ለተሰበሰቡት ምእመናን በተለይም የእንግሊዝ አገር የአየርላንድና የተባበሩት መንግሥታት ተማሪዎችን በማመስገንና፣ ከኬንያና ከናይጀርያ ለመጡት ነጋድያን ልባዊ ሰላምታ በማቅረብ ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ትምህርታቸውን ደምደምዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.