2009-12-16 13:56:00

የሕይወት ባህል እንዲከበር የሚጠይቅ ፊርማ የማሰባሰብ መርሃ ግብር


የኤውሮጳ ኅብረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሕይወት ባህል እንዲከበር የሚጠይቅ ፊርማ የማሰባሰብ መርሃ ግብር በ 27 የኅብረቱ አባል አገሮች ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ በነዚህ አህጉራት RealAudioMP3 ስለ ሕይወት ባህል ትግባሬ የሚጠራው ፊርማ የተሰበሰበበት ሰነድ ክትላትና በስትያ ለኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ጄርዝይ ቡዘክ መሰጠቱ ተረጋገጠ።

የዚህ ፊርማ የሚያሰባስብ ድርገት ሊቀ መንበር ኤርሚና ማዞኒ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፣ በብዙ ሺሕ የሚገመቱት የኤውሮጳ ዜጎች ፊርማቸውን በማኖር ስለ ሕይወት ባህል መረጋገጥ እና መከበር ጥሪ በማቅረብ በኤውሮጳ ህብረት ሕገ መንግሥት እና በህብረቱ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ዘንድ እንዲሰፍር የሚያሳስብ፣ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲከበር ጥያቄው ለህብረቱ አቅርበዋል ሲሉ፣ የኤውሮጳ ሕገ መንግሥት የሚመለከተው ድርገት እና የሕይወት ባህል የሚያነቃቃው እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር የኤውሮጳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ካርሎ ካሲኒ በበኩላቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሕይወት ክብር በማንም የሚጣስ አይደለም፣ ይህ በእሳቸው የሚመራው እንቅስቃሴ እንዲመሠረት ያስገደደበት ጉዳይም ጽንስ ማስወረድ መብት ተድርጎ የሞት ባህል የሚያነቃቁ አካላት የሚያረማምዱት የሞት ባህል መሆኑ ገልጠው፣ በተለያዩ የስነ ምርምር ዘርፍ ሕይወት ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት አወንታዊ እስከ ሆነ ድረስ የሚደገፍ ነው፣ ሕይወትን ጸጋ መሆኑ እና ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት መከበር አለበት ማንም የሕይወት ባለ ቤት አይደለም ስለዚህ ይህ ስለ ሕይወት ጥበቃ እና መከበር የተሰባሰበው ፊርማ የሕይወት ባህል የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.