2009-12-16 13:57:59

ከቻይና ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በቻይና የኪያቲን ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማተዮ ሉ ዱሺ ባደረባቸው የልብ ሕመም ምክንያት በ 91 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለጠ። ብፁዕ አቡነ RealAudioMP3 ዱሺይ እ.ኤ.አ. ሓምሌ 2 ቀን 1919 ዓ.ም. በሬንሹዋ ከተማ ተወልደው ከ 1931 ዓ.ም. እስከ 1935 ዓ.ም. በዪቢን በሚገኘው አነስተኛ ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ቀጥለውም ከ 1935 እስከ 1940 ዓ.ም. ሻውሚንግ በሚገኘው በአቢይ ዘርአ ክህነት ፍልስፍና ቀጥለው እስከ 1950 ዓ.ም. በባይሉ ቼንግዱ አቢይ ዘርኣ ክህነት የቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከ1951 እስከ 1980 ዓ.ም. ወደ ትውልድ መንደራቸው በመመለስ በግብርና ሙያ ተጠምደው ቆይተው በ 64 ዓመአት እድሚያቸው እ.ኤ.አ. በ 1983 ዓ.ም. የክህነት ማዕርግ ተቀብለው በሌሻን ሰበካ በማገልግል ላይ እያሉ በ 1985 ዓ.ም. የሰበካው ሃዋርያዊ አስተዳዳሪ እንዲሆኑ ተሹመው እ.ኤ.አ. በ 1993 ዓ.ም. የጵጵስና ማዕርግ ተቀበልው ለራሳቸው ሳይሳሱ የሰበካው ብቻ ሳይሆን የቻይና ካቶሊኮች በሁሉም መስክ በተለይ በሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በመደግፍ ለእግዚአብሄር መንግሥት መስፋፋት እና ለሁሉም ክብር ያገለገሉ መሆናቸው ከቻይና ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተላለፈልን ዜና ያረጋገጣል።

ብፁዕ አቡነ ማተዮ ሉ ዱሺ በክርስትያን ምእመናን በክልሉ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ጭምር አቢይ ተደናቂነት የነበራቸው ውድ የቤተ ክርስትያን ልጅ መሆናቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.