2009-12-16 13:57:02

ኢራቅ፣ ክርስትያን እና እስላም በጋራ ለሰላም


በኢራቅ ኩርኩክ ከተማ የሚኖሩት ክርስትያን እና ሙስሊሞች በጋራ በዚህ የላቲን ሥርዓት የምትከለው ቤተ ክርስትያን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ለማክበር እየተዘጋጀችበት ባለው የምጽአት ወቅት በጋራ በዚሕች RealAudioMP3 አገር ሰላም እንዲረጋገጥ ይኸንን የሚያነቃቃ መርሃ ግብሮች እያካሄዱ መሆናቸው የኪርኩክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊስ ሳኮ መግለጣቸው ሲር የዜን አገልግሎት ካሰራጨው የዜና ምንጭ ለማወቅ ተችለዋል።

ባለፈው ወር ሚስሊሞች ባከበሩት የኢድ አል አድሃ በዓል የኪርኩክ ክርስትያን ምእመናን ወደ ተልያዩ እስላም ቤተሰብ በመሄድ እንኳን አደረሳቸሁ በማለት ድጋፍ እና እርዳታ ለሚያሻቸው ሚስሊሞች አስፈላጊ ትብብር በማድረግ የወንድማማችነት መንፈስ መመስከራቸው ብጹዕ አቡነ ሳኮ ገልጠው፣ የሃይማኖት ትብብር የሰላም መሠረት መሆኑ እንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን የምታነቃቃው ክብር ገቢራዊ ለማድረግ የሞከረ መርሃ ግብር ነው እንዳሉም የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።

በኢራቅ ሰላም እንዲረጋገጥ ዓለም አቀፍ የሰላም ጸሎት በአረብኛ በኩርድ በሶርያ እና በቱርክሜን ቋንቋዎች ተተርጉሞ ሁሉም እዲደግመው ብሎም እግብር ላይ እንዲያውለው የኩርኩም ሚስሊሞች እና ክርስትያን ምእመናን በጋራ አቢይ የትብብር ጥረት እያደረጉ ናቸው ብለዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለም በኢራቅ ኪርኩክ ከተማ የሚገኙት የካቶሊክ ደናግል ማህበር አባላት፣ በዚህ የምጽኣት ወቅት በድኽነት ለሚሰቃየው የክልሉ ሕዝብ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ላይ መሆናቸው ሲር የዜና አገልግሎት በማሳወቅ አክሎም ድኾች አቢያተ ክርስትያን እንርዳ የተሰኘው ዓለም አቅፍ የክርስትያን ግብረ ሰናይ ማኅበር እነዚህ የኢራቅ የደናግል ማኅበራት ለሚያነቃቁት የትብብር መርሃ ግብር ድጋፍ 25 ሺሕ ኤውሮ መሰጠቱ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.