2009-12-16 13:53:00

ሚሥጢረ ተክሊል እና ስለ ዱቁና ማዕርግ አዲስ ውሳኔ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባላቸው የመንበረ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሠረት በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሕገ ቀኖና ዘንድ ስላለው ስለ ሚሥጢረ ተክሊል እና ማዕረገ ዱቁና የሚመለከተውን አንቀጽ በመከለስ በአንቀጹ የሠፈሩ RealAudioMP3 አንዳንድ የውሳኔ ቃላቶች እንዲቀየር ማድረጋቸው ተገለጠ።

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በመንበረ ጴጥሮስ በነበሩበት ወቅት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስለ ማዕርገ ዱቁና እና ሚስጢረ ተክሊል የሚመለከቱት ሁለት ጥያቄዎች ጥናት ሲደረግባቸው ቆይቶ ከረዥም ዓመታት በኋላ ሲጠበቅ የነበረ ውሳኔ መወሰዱ ጉዳዩ ከቅድስት መንበር የተላለፈ መግለጫ ይጠቁማል።

በሕገ ቀኖና ዓናቅጽ 1008 እና 1009 በጵጵስና በክህነት እና በድቁና ማዕረጎች መካከል ያለው ልዩነት ለይቶ በማሳወቅ፣ ሆኖም እነዚህ ማዕርጐች የክርስቶስ ተግባሮችን የሚወክሉ በእርሱ ስም የሚፈጸም ተግባር ቀጣይነቱን የሚያመለክት መሆኑ የስነ ሕግ ጉዳይ የሚመለከት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ኮኮፓልመሪዮ በተላለፈው መገልጫ ጠቁመው፣ እነዚህ ማዕርጎች በክርስቶስ ስም ክርስቶስን ወክሎ በቅድሴ ሥነ ሥርዓት የወንጌል ቃል በማስተማር ግብረ ሰናይ በመፈጸም ለእግዚአብሔር ሕዝብ የሚቀርብ አገልግሎት የሚመለከት መሆኑ ሲያብራሩ፣ የሕግ ጉዳይ የሚመለከተው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኹዋን ኢግናዚዮ አሬታ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱ ቃለ ምልልስ፣ ሁለተኛው እንዲሻሻል የተደረገው እርሱም ሚሥጢረ ተክሊል የሚመለከተው በአንቀጽ 1087 በ 1117 እና በ 1124 ዘንድ ሰፍሮ ያለው በማስደገፍ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ከቤተ ክርስትያን የራቀ ግኑኝነት ያቋረጠ የሌሎች የሴራ ቡድኖች አባል የሆነ ሚስጢረ ጥምቀት ግን የተቀበለ ክርስትያን ምእመን ትዳር ለመመሥረት ሚስጢረ ተክሊል በቤተ ክርስትያን መቀበል አለበት ከሚለው ግዴታን ከሚያሳስብ አንቀጽ ነጻ ናቸው አይመለከታቸው የሚለውን ቃል ቅዱስ አብታችን በመቀየር፣ ሚሥጢረ ተክሊል በቤተ ክርስትያን መቀበል አለበት የሚለው ግዴታዊ ውሳኔ ይመለከታቸዋል የሚል ሲሆን፣ ሆኖም እነዚህ ከቤተ ክርስትያን ወጥተው የነበሩት ሚሥጢረ ተክሊል የተቀበሉት ዳግም ወደ ቤተ ክርስትያን ለመመለስ ያላቸውን ፈቃድ መሠረት ዳግም የትምህርተ ሃይማኖት ሕንጸት ይኸንን የሚመለከተ ሃዋርያዊ ኖልዎ ሊያገኙ እንደሚገባ ያመለክታል ብለዋል።

ከቤተ ክርስትያን የወጡ እራሳችውን ከቤተ ክርስትያን ያራቁ እና የተገለሉ በመንግሥት የከተማ ምክር ቤቶች ዘንድ ብሔራዊ ጋብቻ ቢመሠርቱም ቤተ ክርስትያን ይኽ ጋብቻ እንደማትቀበለው ነው፣ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ያሻሻሉት አዲሱ ሕገ አንቀጽ እነዚህ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስትያን እንዲመለሱ የሚያበረታታ የሚፈጽሙት ጋብቻ ሕጋዊነት እንዲኖርረው የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.