2009-12-14 14:39:36

የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት በቅድስት መሬት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ወር እዚህ ሮማ የተካሄደው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ይፋዊው ሲኖዶስ ወቅት፣ በአፍሪቃ ያለሽው የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆንሽው ቤተ ርክስትያን ተነሽ RealAudioMP3 በማለት የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ማነቃቃታቸው እና ያላት ኃላፊነትም የሚያሳስብ ጥሪ ማቅረባቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ይኸንን መርህ በማድረግ ከ 30 የአፍሪቃ አገሮች የተወጣጡ 83 ብፁዓን አቡናት እና 7 ሊቃነ ጳጳሳት በአፍሪቃ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዳግም ለማነቃቃት በኅብረት ቅድስት መሬት በሚገኘው በጋሊለያ የጉባኤ አዳራሽ በአፍሪቃ ስላለው ስብከተ ወንጌል ርእስ በማድረግ ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸው ተገልጠዋል።

በአፍሪቃ የሚረጋገጠው አስፍሆተ ወንጌል በአፍሪቃ ያለው ማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ አቢይ ግምት የሚሰጥ የሰውል ልጅ የተሟላ እንድገት የሚያንቃቃ የሰውን ልጅ መብት እና ፍቃድ በማክበር ሰላም እርቅ እና ፍትሕ ለማረጋጥ የሚገፋፋ መሆን እንዳለበት ብጹዓን ጳጳሳቱ ባካሄዱት ስብሰባ አስምረውበታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.