2009-12-14 14:36:37

እግዚአብሔርን በተስፋ የመጠባበቅ ፍላጎት


ትላትና ከሰዓት በኋላ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ለጥቀ አባ ዣን ላፊተ ጳጳሳዊ የፍትሕና ሰላም ምክር RealAudioMP3 ቤት ዋና ጸሓፊ ለጥቀ አባ ማሪዮ ቶሶ እና ለጥቀ አባ ጆቫኒ የአኩይላ ተባባሪ ጳጳስ እንዲሆኑ ለተጠሩት ማእርገ ጵጵስና ሰጥተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት ባሰሙት ስብከት አቡን እግዚአብሔርን በተስፋ የመጠባበቁ ፍላጎት የሚያነቃቃ በእያንዳንዱ አማኝ ልብ ዘንድ ይህ ፍላጎት ጎልቶ እንዲረጋገጥ የሚመራ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው ብለዋል። ሰው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ ሰውን የሚጠባበቀው እግዚአብሔር፣ ለመቀበል ለማስተናገድ እና ፍቅሩን ተቀብሎ የሕይወት መሪ ለማድረግ አቡን ይኸንን ለማረጋገጥ የሰውን ልጅ በር ለሚያንኳኳው እግዚአብሔር የሰው ልጅ በሮቹን ይከፍት ዘንድ የሚያነቃቃ የሚመራ በቃል እና በሕይወት የሚያስተምር ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.