2009-12-14 14:35:09

ብቃት ያለው ቀልጣፋው ኤኮኖሚ እና የተሟላ የሰው ልጅ እድገት


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፍ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ማዘጋጃ ምክንያት ለኢጣሊያ የኢንዳስትሪ ማኅበር ያመራር አካላት እና ሠራተኞች የተሳተፉበት ባቀርቡት ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ የሰው ልጅ በኤኮኖሚ አይለካም ይህ ማለት ደግሞ የሰው ልጅ የተሟላ እድገት የማያነቃቃ እና የማያረጋገጥ ኤኮኖሚ አወንታዊ ውጤት RealAudioMP3 ይኖረዋል ማለት ዘበት ነው ብለዋል።

ብፁዕነታቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ጉዳይ ትምህርት ጠቅላይ ሐሳብ በመጥቀስ የአንድ ኤኮኖሚ ብቃት በሚሰጠው ገቢ ወይንም የሚያስገኘው ከፍተኛ ምርት ብቻ አይለካም የሰው ልጅ የተሟላ እድገት ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆን ይገባዋል፣ ካሉ በኋላ የክርስትናው እምነት ስሜታዊ ከዕለታዊው ተጨባጩ ሕይወት፣ ከኃላፊነት ለማምለጥ የሚያገለግል መሣሪያ ሳይሆን፣ ተጨባጩን ዓለም በመኖር በፍቅር እና ለእምነት ታማኝ በመሆን ኃላፊነትን በመወጣት በወንጌላዊው ተስፋ በመመራት ውጤታማ ለማድረግ የሚያበቃ በተግባር የሚገለጥ ነው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።

ሥጋ ለብሶ በመካከላችን የተገኘው እግዚአብሔር ሰብአዊነታችንን አዲስ ስብእና በማልበስ አዲስ ሰብአዊነት ያረጋገጠ ነው። ይህ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው እግዚአብሔር ወደ እውነተኛው ክርስትያናዊ እሴታዎች ይመራናል በእለታዊ ኑሮአችን እግብር ላይ እንድናውለም ይደግፈናል ብለዋል። ወንጌላዊው እውነት ሰብአዊነት የተካነው የሰለጠነ የሰው ልጅ ክብር ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚያነቃቃ እና የሚንከባከብ እንዲከበር የሚገፋፋ እና የሥራ እና የሙያ እውነተኛው ፍጻሜውን የሚያመለክት ባህል እንዲጨበጥ ያደርጋል፣ ስለዚህ ክርስትያን አምራች ዜጋ የኤኮኖሚ ባለ ሙያ ይኸንን ባህል በዕለታዊ ኑሮው እግብር ላይ የሚያውል ነው እንዳሉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.