2009-12-14 14:37:56

ስለ እግዚአብሔር የሚመለከቱ ጥያቄዎች


እግዚአብሔር ዛሬ፣ ከርሱ ጋር እና አለ እርሱ ሁሉም ይቀየራል የሚል ጥያቄ ርእስ በማድረግ ከባለፈው ሓሙስ ጀምሮ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያነቃቃው ዓቢይ ቲዮሎጊያዊ እና ፍልስፍናዊ አውደ ጥናት RealAudioMP3 ሮማ በሚገኘው የአውዲቶሪዩም የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ ይህ ባለፈው ቅዳሜ የተፈጸመው አውደ ጥናት የቲዮሎጊያ እና የፍልስፍና ሊቃውንት ጋዜጠኞች ምሁራን የባህል አካላት የመናብረተ ጥበብ አስተማሪዎች የፖሊቲካ አካላት፣ በጠቅላላ 1500 ተጋባእያን ስለ እግዚአብሔር ጥያቄ በማንሳት የተወያዩበት መድረግ እንደነበር ሲገለጥ፣ ሮማ የሚገኘው ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ እና ጳጳሳዊ የሕይወት ተቋም ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ ፖለትካ፣ ስነ ጥበብ እና ስነ ጽሕፉ ስለ እግዚአብሔር የሚያቀርቡት ጥያቄዎች ምን እንደሚመስል እንዴት ባለ መልኩ እንደሚያቀርቡት በመዳሰስ ሰፊ እና ጥልቅ አስተምህሮ ማቅረብቸው ተገልጠዋል። እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚገፋፋው እውቀት በሰው ልጅ ዘንድ ያለ ብቻ ሳይሆን፣ የሚሰጥ ለሰው ልጅ የተሰጠ ጸጋም ነው፣ የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ለማወቅ ስለ እግዚአብሐር ጥያቄ ለማቅረብ የሚችል እና የዚህ ኅላዌ ምልክት እና ዱካ በውስጡ ያለው ሆኖ የተፈጠረ ቢሆንም ቅሉ፣ ይህ ምልክት ጸጋ መሆኑ መዘንጋት የለብንም ብለዋል።

ወደ እውነት የሚመሩ የተለያዩ መንገዶች አሉ እነዚህ መንገዶች ከእግዚአብሔር የመገለጽ ፈቃድ ከእምነት እና ከምርምር የሚገኙ ናቸው፣ ሆኖም እነዚህ መንገዶች የተለያዩ ቢመስሉም፣ ወደ አንዱ እና ብቸኛው ወደ ሆነው እውነት የሚመሩ ናቸው። ሆኖም እነዚህን መንገዶች የሚያገል እየተስፋፋ ያለው ሁሉም ያው ነው፣ እግዚአብሔር ቢኖርም ባይኖርም ያው ነው፣ የእሴቶች ቅደም ተከተል ብሎ የለም የሚለው ባህል፣ የእግዚአብሔር ኅልውና የሚገልጡ የሚያረጋግጡ የሚጸነሱ ሐሳቦች መላ ምቶች ቅድመ እውቀት በጠቅላላ መላ ምት ሆነው ብቻ እንዲቀሩ የሚገፋፋው ባህል፣ ሰው የሁሉም መመዘኛ እና ማእከል ነው ከሚለው ባህል የመነጨ መሆኑ አብራርተው፣ ይህ ባህል የሰው ልጅ በተስፋ ቢስነት እንዲዋዥቅ ብሞትም ብኖርም ያው ነው በሚለው መንፈስ እንዲመራ በማድረግ፣ አበይት ለሚባሉት የሕይወት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ያማይችል እንዲሆን እያደረገ በደመ ነፍስ እንዲኖር ከማድረጉም አልፎ ያዘነ ፍጡር ሆኖ እንዲኖር እያደረገው ነው፣ ይህ ጉዳይ የሰው ልጅ መልሶ ስለ እግዚአብሔር ለመጠየቅ ዳግም እንዳስገደደውም የተረጋገጠ ነው፣ እግዚአብሔር የሚለው አነጋገር እና መላ ምት ስለ እግዚአብሔር ኅልውና ከመጠይቅ ነጻ አያወጣም ብለዋል።

ከእግዚአብሔር የሚያርቀው መንገድ መልስ ባለ መሆኑም መልሶ ስለ እግዚአብሔር ለሚቀርበው ጥያቄ ይገፋፋል አሳልፎም ይሰጣል፣ ስነ ምርምር ለብቻው መልስ እንደማይሰጥ የሚያረጋገጥ ነው፣ ስለዚህ ለማመን ብርታት ይጠይቃል ብለዋል።

በጉባኤው እግዚአብሔር በተመለከተ የሰው ልጅ የሚያቀርበው ጥያቄ በቲዮሎጊያ እና በፍልስፍና በመዳሰስ ንግግር ያሰሙት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀመንበር የነብሩት ብፁዕ ካርዲናል ካሚሎ ርዊኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሕይወት በባህል ባህል ደግሞ በሕይወት ላይ የተደገፈ ነው። ይህ በባህል እና በሕይወት መካከል ያለው የመደጋገፍ ሂደት፣ በሁለቱም ዘንድ ያለው ጥልቅ ግኑኝነት የሚያመለክት ሲሆን በባህሉ መድረክ የክርስትና ኅላዌ ለአስፍሆተ ወንጌል ወሳኝ ነው ብለዋል።

እምነት የልብ የስሜት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ባህሎችን በጥልቀት የሚነካ የሚጠይቅ የባህል መሠረቱን የሚያናጋ መሆን ይገባዋል፣ ስለዚህ እምነት ስሜታዊ ብቻ ሳይሆን ስነ ጥበባዊም ጭምር ነው። ብዙውን ጊዜ ባህሎች ከዚህ ጥያቄ ለመሸሽ ሲራወጡ ይታያል፣ ሆኖም ለመሸሽ የሚደረግ ሩጫ መልሶ ወደ መሠረታዊው ጥያቄ ፊት እንዲቆሙ ያስገድዳል፣ ስለዚህ ክርስትና ባለው ጥልቅ ባህል መሠረት ከባህሎች ጋር የሚወያይ እና ባህሎችን ወደ ሙላት የሚመራ ነው ብለዋል።

በእግዚአብሔር ለማመን እግዚአብሔርን ለመቀበል እና በመጨረሻም ቤተ ክርስትያን የምታቀርበው የስነ ሃይማኖት ትምህርት እና አንቀጸ ሃይማኖት በመቀበል እምነትን በሙላት መኖር አስፈላጊ ነው። በእግዚአብሔር አምናለሁ ብሎ ብቻ መቅረቱ እግዚአብሔር መቀበልን አያረጋግጥልንም፣ መወለድ እና መሞት የሕይወት መጀመሪያ እና መደምደሚያ አይደለም ይህ ደግሞ እውነተኛው እና ሓቀኛው ክርስትና የክርስቶስን ትምህርት መሠረት በማድረግ የሚያስተምረው ትምህርት ነው፣ ክርስቶስ የሰብአዊነት ሙላት ብቻ ሳይሆን የሰብአዊነት አዳሽም ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.