2009-12-11 14:35:15

የሰብአዊ መብት ጥበቃ ዓቢይ ሚና መጫወት


የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ብሎም በሁሉም ዘንድ እንዲከበር በማነቃቃት ረገድ ዓቢይ ቢና ለሚጫወቱት እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በመለየት እና በመረጥ የምትሰጠው ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የተሰየመው ሽልማት RealAudioMP3 ከትላንትና በስትያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለአንድረ ክሉክስማን በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ከተካሄደው የረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንዳበቁ በተዘጋጀው ልዩ በዓል መስጠታቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር እለታዊ ጋዜጣ አስታወቀ።

ይህ ሽልማት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መከበር እና ሰውን ማእከል ያደረገ በር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የተሰጠው ትምህርት እና አብነት መሠረት በማድረግ ይህ ባህል በቃል እና በሕይት በማነቃቃት እና በማስፋፋት ረገድ ዓቢይ ሚና የሚጫወቱትን በመለየት የላቀውን በመምረጥ የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን፣ ሽልማት በተሰጠበት ስነ ሥርዓት የተሸላሚ መራጭ ዳኞች አባላት ከሆኑት ውስጥ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንሲዘክ ማቻርስኪ የስነ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተቋም ሊቀ መንበር እና ሽልማቱን ያነቃቁት አንድረይ ዞሎ እና ዋልደማር ራታጅ መሳተፋቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.