2009-12-11 15:54:15

የረፓብሊክ አይርላንድ ጳጳሳት መግለጫ .


የረፓብሊክ አይርላንድ ረኪበ ጳጳሳት በመይኑት ከተማ እተካሄደ መሆኑ ከዳብሊን ተመለከተ፡ በዚሁ ከርእሰ ከተማ ዳብሊን የደረሰ ዜና መስሠረት የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ፡ የመንግስት መርፊ ኮሚስዮን በዳብሊን ሀገረ ስብከት አንዳንድ ካህናት በሕጻናት ላይ ፈጸሙት የተባለው የፍትወተ ስጋ አመጽ አጣርቶ ይፋ ያደረገውን ሪፖርት መመልከታቸው ተነግረዋል።የረፓብሊክ አይርላንድ ጳጳሳት ጉዳዩን ካጠና እና ከተነጋገሩበት በኃላ ፡ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጠው በይፋ ይቅሬታ የሚጠይቅ መግለጫ ይፋ ማደርጋቸው ይህ ከዳብሊን የመጣ ዜና አስታውቀዋል።ይሁን እና የረፓብሊክ አይርላንድ ረኪበ ጳጳሳት ፡ በዳብሊን ሀገረ ስብከት ዓመጽ የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ቤተሰቦቻቸውን በይፋ ይቅሬታ ጠይቀዋል።

ሀገረ ስብከቱ የተፈጸመውን ዓመጽ ከማጋለጥ ፈንታ ለብዙ ግዜ መሸፈኑ የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት በሀገረ ሰብከቱ ላይ ሂስ መሰንዘሩ አብሮ የደረሰ ዜና ገልጸዋል።

የሀገሪቱ ቤተክርስትያን ለመንፈሳዊ ተሐድሶ እና ሥነ ምግባር አስፈላጊውን ርምጃ እንደምትወስድ ነው የረኪበ ጳጳሳት መግለጫ ያሚያስገነዝበው። የተፈጸመው አሳፋሪ እና አስከፊ ተግባሩ ማውገዛቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የዚሁ አሳፋሪ ተግባር ሁኔታ በቅርብ ለመረዳት የረፓብሊክ አይርላንድ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሲን ብረዲ የዳብሊን ሊቀ ጳጳስ ዲይርሙይድ ማርቲን በረፓብሊክ አይርላንድ የቫቲካን ሐዋርያዊ ወኪል ወደ ቫቲካን መጥራታቸው እና ዛሬ አንሻቸው ከነሱ ጋር ተገኛኝተው በጉዳዩ እንደሚነጋገሩ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.