2009-12-11 14:39:45

ቤተ ሰብ ከብኩንነት እና ከቦዘኔነት መንፈስ ማዳን


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ባለፈው ማክሰኞ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም ማክበሯ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚያኑ እለት እዚህ በኢጣሊያ ሎሬቶ በሚገኘው የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥፍራ RealAudioMP3 የቫቲካን ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ የመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ መቅረቡ ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት ይህ ቅዱስ ሥፍራ የቤተሰብ ክብር እና እሴቶች እንዳይጣሱ እንዳይረሱ እንዳይካዱ የሚያሳስብ የቅድስት ቤተሰብ ሥፍራ ነው። ልቅ እና ኃላፊነተ አልባ የሆነው ነፃነት በሚያስፋፋው ባህል ምክያታዊ ተደርጎ በሚቀርበው እኔነት ማእከል ማድረግ አለ መታመን መዋከብ የመሳሰሉት ጸረ ቤተሰብ ልምዶች አቢይ ችግር እያስከተለ መሆኑ ገልጠው፣ ቤተሰብ የተቀደሰው ጥሪው ዳግም ይላበስ ዘንድ የቅድስት ቤተሰብ ድጋፍ ያሻዋል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በሁሉም የላቲን ሥርዓት በሚከተሉት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ይህ በአለ ጽንሰታ ለማርያም በዚህ የክህነት ዓመት በሚታሰበበት ወቅት ደምቆ መከበሩ ሲገለጥ፣ ፊደስ የዜና አገልግሎት እንዳመለከተው በቻይና በሻንግሃይ ካቴድራል 5 ሺሕ ምእመናን የተሳተፉበት ብፁዕ አቡነ ጁዜፐ ክሲንግ ወን ዝሂ በ 130 ካህናት ታጅበው በመሩት መሥዋዕተ ቀዳሴ ለ 11 የዘርአ ክህነት ዲያቅናት የክህነት ማዕርግ መስጠታቸው ለማወቅ ተችልዋል።

እንዲሁም በ ታይ ዩአን ሰበካ 106 ካናት ባጀበቱ 2 ሺሕ ምእመናን በተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ 6 ሲያቆናት የክህነት ማዕርግ መቀበላቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.