2009-12-11 15:06:52

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጋቦን መራሄ መንግስት ፕረሲዳንት ዓሊ ቦንጎ ተቀብለው አነጋገሩ.


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጋቦን መንግስት መራሄ መንግስት ፕረስደንት ዓሊ ቦንጎ ኦንዲምባ በቤት ጽሕፈታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን መግለጫ አስታወቀ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የጋቦን መሪ ፕረሲደንት ዓሊ ቦንጎ ኦንዲምባ በቅድስት መንበር እና በጋቦን መካከል ያለውን ግኑኝነት የጋቦን ካቶሊካውያን ለጋቦን ህዝብ እድገት በተለይ በትምህርት ዘርፍ በኩል የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ትኩረት በመስጠት ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል።

በዚሁ ቫቲካን ውስጥ የወጣ መግለጫ መሠረት ፡ ቅሱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የጋቦን ፕረሲደንት በቅረቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ የፕረሲዳንቱ አባት ኤል ሐጅ ኦማር ቦንጎ በመዘከር ተወያይተዋል።

የጋቦን መንግስት መሪ ፕረሲደንት ዓሊ ቦንጎ ኦንዲምባ ከየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና ከየውጭ ጉጋይ ዋና ተጠሪ ከሊቀ ጳጳሳት ከብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር ተገናኝተው በተመሳሳይ የሐሳብ ልውውጥ ማድረጋቸው የቫቲካን መግለጫ አመልክተዋል።

ቫቲካን እና አፍሪቃዊት ጋቦን እኤአ በ1997 እኤአ ሁለገባዊ ስምምነት መፈራረማቸው መግለጫው አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.