2009-12-09 15:36:47

አብሮሲያኑም ቤተ መጻሕፍት


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ ትላትና በላቲን ሥርዓት የተከበረው በዓለ ፅንሰታ ንጽሕት ድንግል ማርያም እና በዚያኑ እለት በሚላኖ በብጹዕ ካርዲናል ፈደሪኮ ቦሮመዮ የተመሠረተው 400ኛውን RealAudioMP3 የምሥረታ ዓመቱ እያከበረ ያለው የሚላኖ የቅድስ አምብሮዚዮ ቤተ መዝገብ ምክንያት፣ ሚላኖ በሚገኘው በመንበረ ጳጳስ ቤተ ክርስትያን ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በሚላኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዲዮኒጂ ተታማንዚ ታጅበው ማቅረባቸው ተገልጠዋል።

በኤውሮጳ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋሙት ቤተ መዛግብት ውስጥ ይህ የሚላኖው የቅዱስ አምብሮዚዮ ቤተ መዝገብ በታሪክ ሁለተኛ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል በርቶኔ በቅዳሴው ስነ ሥርዓት ባሰሙት ስብከት፣ ንጽሕት ድንግል ማርያም፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተለይታ እና ተመርጣ ለዚህ እግዚአብሔር ላዘጋጀላት እቅድ ታማኝ ብቻ ሳትሆን፣ እንዳልከው ይሁንልኝ በማለት በእግዚአብሔር ፍቅር ተመርታ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት በመሆን የእግዚአብሔር ምህረት እንዲጎበኘን የእግዚአብሔር የመዳን እቅድ ተካፋይ ሆናለች፣ ካሉ በኋላ፣ የአዳም ኃጢኣት ያልነካት በግብረ ገብ እና በስነ ምግባር የተካነች በግብረ ገብ እና በሥነ ምግባር የመኖር አብነት የሆነች ጸጋ የሞላት ነች ብለዋል።

ማርያም የፍጹም ሰው አብነት የሆነው የፍጹም ሰው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሆነው የእግዚአብሔር እናት ንጽሕናዋ የተሟላ ጊዜ እና ቦታ ታሪክ የማይሽረው መሆኑም ገልጠው፣ በኃጢኣት ምክንያት ከኛ የራቀው የፍጹም ሰው እናት ሆና ደስ ይበልሽ የተባለች የዚህ የመዳን እቅድ ዋና ተካፋይ በመሆኗ ደስ ያላት እናት ነች በማለት ወደ እርሷ ቀርበን ከርሷ ጋር እና በእርሷ አማላጅነት የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ ስለ ጎበኘን ደስ እንሰኝ ብለዋል።

በመጨረሻም የሚላኖው የቅዱስ አምብሪዚዮ ቤተ መዝገብ እ.ኤ.አ. በ 1609 ዓ.ም. በብፁዕ ካርዲናል ፈደሪኮ ቦሮመዮ መመሥረቱንም ዘክረው ሚላኖ የባህል የሳይንስ እና የቲዮሎጊያ ማእክል እንዲትሆን ያበቃት ጸጋ ነው ብለዋል።

በፁዕ ካርዲናል በርቶነ በዚህ አጋጣሚም በቅዳሴው ስነ ሥርዓት እና በቤተ መዝገቡ የምሥረታ ዓመት በተዘጋጀው በዓል ከተሳተፉት ከኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ጋር ተገናኝተው፣ ቤተ ክርስትያን ለሰው ልጅ ሓቅ ከማበሰር እትቆጠብም ሲሉ፣ ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ ቤተ ክርስትያን የብጹእነታቸው ቃል በማስተጋባት ቤተ ክርስትያን እጅግ አስፈላጊ ነች ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.