2009-12-09 15:34:50

ታማኝ የእግዚአብሔር ፍቅር ምስክር


በላቲን ሥርዓት ትላንትና በዓለ ፅንሰታ ንጽሕት ድንግል ማሪያም መከበሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ትላትና ለስፐይን እና ለላቲን አሜሪካ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 በስፐይን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ረንዞ ፍራቲኒ ፊርማ የሰፈረበት መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጠ።

ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም ታማኝ የእግዚአብሔር ፍቅር ምስክር መሆኗ በማብራራት፣ ማርያም ንግሥት የመድኃኔ ዓለም የመኃሪው እናት መሆኗ ሰላም ላንቺ ይሁን የሚለው ማርያማዊ ጸሎት በጥልቅ እንደሚያረጋገጥልን አመልክተዋል። የእግዚአብሔር መኃሪነት የሰውን ልጅ በፍቅር የፈጠረው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ዘወትር ታማኝ በመሆን የተጫወተችው ዓቢይ ሚና በመጥቀስ፣ የማሕጸንሽ ፍሬ ኢየሱስን እንድታሳየን ማርያምን በመማጠን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርተን በዚህ የእግዚአብሔር ምኅረት እጅግ በተጠማው ዓለም ከዚህ ፍቅር በመነጨው የርስ በርስ መዋደድ እና ከእግዚአብሔር ጋር ቅን ግኑኝነት እንዲኖረን የሚያበቃ የእግዚአብሔር ፍቅር መስካሪዎች እንድንሆን ጸልየው ይኸንን ለመፈጸም ለሚያበቃን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ታማኞች እንድሆን እርጂን ብለዋል።

በመጨሻም እ.ኤ.አ. 2011 ዓ.ም. በማድሪድ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲሸኝ በካቴድራል አልሙደና ትላትና በበዓለ ጽንሰታ የማድሪድ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ሩዎኮ ቫረላ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት መጸለያቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.