2009-12-09 15:39:27

ምጽአት ለልደት ማዘጋጃ እና ልባችን ለተስፋ የምንከፍትበት ወቅት ነው


ቅዱስ አጎስጢኖስ ተነስ እግዚአብሔር ላንተ ሲል ሰው ሆኗል በማለት ስለ ምጽአት በሰጠው ስብከት የሰፈረው መንፈሳዊ ቃል መርህ በማድረግ፣ የኢጣሊያ ቤተ ክርስትያን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በመዘጋጀት RealAudioMP3 ላይ መሆኗ ሲገለጥ። የሬጆ ካላብሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪቶሪዮ ሞንደሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዓለም ማኅበርሰብ ዘንድ አቢይ ችግር ሆኖ ያለው በመካከላችን ያለው እና ሰው ሆኖ ወደ እኛ የሚጣውን እግዚአብሔር አለ ማየት መሆኑ ጠቅሰው፣ የዚህ ችግር መንስኤ ደግሞ እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔርነቱ ሳይሆን እኛ እንደምንሻው እና እኛ በምናቀርበው መመዘኛ ለኛ በሚስማማ መንገድ ለመፈለግ ስለ ምንራወጥ ነው፣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔርነቱ እንደ ራሱ መቀበል እና በርሱ ፈቃድ መመላለስ ያስፈልጋል፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በማያዳግም ሁኔታ የተገለጠው እግዚአብሔር መቀበል የደስታ የሰላም የመግባባት የመቀራረብ የመተሳሰብ ወዘተረፈ ምክንያት ነው፣ ስለዚህ ምጽኣት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመቀበል እና በእርሱ ከእግዚአብሔር ለታደል ተስፋ ልባችንን ለመክፈት የምንዘጋጅበት የተቀደሰ ወቅት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.