2009-12-07 16:11:03

የር.ሊ.ጳ የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር አስተምህሮ


በላቲን ሥርዓተ አምልኮ ግጻዌ የትናንትና እሁድ የዘመነ ምጽአት ሁለትኛ እሁድ በመሆኑ፣ ቅዱስነታቸው ሥጋ የለበሰና መሃከላችን ያደረ ቃለ እግዚአብሔር በሰው ታሪክ ውስጥ መሀከለኛ ቦታ በመያዝ ሕይወታችንን መምራት እንዳለበት አስምረውበታል። ኃጢአት ዘወትር የቤተ ክርስትያን አባሎችን በክፋት ወጥመድ ውስጥ እንዲያገባ ስለሚታገል ሁሉ ጊዜ መንጻት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው ዛሬ በኮፐንሃገን በሚጀመረዉ የአለማችን ሙቀት መጨመር በሚመለከት ለመወያየትና ሁነኛ እርምጃ ለመውሰድ በተባበሩት መንግሥታት የተጠራ የከባቢ አየር ለዉጥ ጉባኤን የሚመለክት መልእክትም አስተላልፈዋል። በዚሁ ጉባኤ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች “ፍጥረት ሁሉን የሚያከብርና በሰው ልጅ ክብር የተመሠረተ ሁለመናዊ ሥልጣኔን የሚያዳብርና ለጥቅል በጎ ነገር መሆን” እንዳለበት ማስታወስ እንደሚያስፈልግ ገልጠዋል።

እንዲሁም “ተፈጥሮን ለመንከባከብ እያንዳንዳችን ልዩ በሆነ መንገድ ለድሆችና ለሚመጣው ትውልድ በማሰብ ተገቢ የኑሮ ህይወት በመኖር ሓላፊነት መሸከም አለብን፣ ጉባኤው እንዲሳካና ውጤት እንዲንረው ከተፈለገ፣ ባለበጎ ፈቃድ የሆኑ ሰዎች ሁላቸው በእግዚአብሔር የተሰጠውን የተፈጥሮ ሕግ ማክበርና የሰው ሕይወት ግብረ ገባዊ ትርጉም መገንዘብ ያስፈልጋል።” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን ነጥብ ከመዘርዘር በፊት በዕለቱ ቃለ ወንጌል በማትኮር፣ ወንጌላዊው ሉቃስ ስለ ቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ የዘገበው ጊዜና ቦታ ከስብከቱ ያለውን ግኑኝነት አበክሮ እንደሚገልጥ እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል። “እርግጥ ነው ወንጌላዊው ቅዱስ መጽሓፍን የሚያደምጥ ወይም የሚያነብ የሆነ ልበ ወለድ ነገር እንዳልሆነ ያስገነዝባል፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ታሪካዊ ሰው መሆኑንና በተገለጸው ግዜና ቦታ እንደኖረ ያመለክታል፣” ካሉ በኋላ ወደ ሁለተኛውና ዋናው መልእክት በመሸጋገር ቅዱስነታቸው “ይህ ከላይ ወርዶ በቅዱስ ዮሓንስ ያረፈው የእግዚአብሔር ቃል” መሆኑንም አመልክተዋል።

ይህንን ለማስረዳት ቅዱስነታቸው ዛሬ በዓሉን ከምናከብረው ቅዱስ አምብሮዝዮስ ጽሑፍ በመጥቀስ የሚከተለውን ብለዋል፣ “የእግዚአብሔር ቃል ታሪክን የሚያንቀሳቅስ፣ ነቢያትን አእምሮአቸው የሚከሥት፣ የመሲሑ መንገድን የሚያሰናዳ ቤተ ክርስትያንን የሚሰብስብ ነው። መልኮታዊው የእግዚአብሔር ቃልም ከድንግል ማርያም ሥጋ የለበሰ ራሱ ኢየሱስ ነው፣ በእርሱ እግዚአብሔር በሙላት ተገለጸ፣ እርሱ የእውነቱንና የምሕረቱን መዝገብ በመክፈት ስለ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገረን ሰጠንም። ቅዱስ አምብሮዝዮስ መግለጫውን በመቀጠል፣ ምድረ በዳ የነበረችው ዓለማችን ለእኛ ፍሬ እንድታፈራ ዘንድ ዘለዓለማዊው ቃል ከሰማይ ወደ ምድር ወረደ፣ ይላል።”

ቅዱስነታቸው ትምህርታቸውን ወደ ድንግል ማርያም በማዞር “የቤተ ክርስትያን የመጀመርያዋ ዘርና በዚህ ምድር የእግዚአብሔር ገነት ስለሆነችው እመቤታችን” እንዲህ ብለዋል፣ “ከነገ ወዲያ ንጽሕናዋን የምናስታውሰው ድንግል ማርያም ንጽሕት ስትሆን ቤተ ክርስትያን ግን ኃጢኣት ኣባሎችዋን በክፋት ወጥመድ ለማግባት ስለሚታገል ገና መንጻት ያስፈልጋታል፣ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ሁል ጊዜ እንደ በምድረ-በዳና በገነት መሀከል የማያልቅ ትግል አለ፣ ይህም ማለት ምድርን በሚያደርቅ ኃጢኣትና የቅድስና አመርቂ ፍሬ እንድትሰጥ በመስኖ ውኃ በሚያጠጣ የእግዚአብሔር ጸጋ መሀከል ሁል ጊዜ ቅራኔ አለ። ስለዚህ በዚህ አመርቂ የምጽአት ጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ተመርተን ሕይወታችን እንድናስተካክል ዘንድ እመ አምላክን እንለምን” ብለው በመማጠን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው የመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ካሳረጉ ከተለያዩ ቦታዎች ለመልእከ እግዚኣብሔር ጸሎት ለተሰበሰቡት በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው በሥርዓቱ ለተገኙት ምእመናን ሓዋርያ ቡራኬና ሰላምታ ኣቅርበው ኣሰናበቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.