2009-12-02 14:16:55

እግዚአብሔርን ለመረዳት ንኡስነትህን መገንዘብ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና እዚህ በቫቲካን ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ያለው የዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት ይፋዊ ጉባኤ በመሳተፍ ለሚገኙት የቀረበውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፣ RealAudioMP3 እውነተኛው የቲዮሎጊያ ሊቅ ባለው የምርምር ብቃት የእግዚአብሔር ሚስጢር ለመለካት እና ብዙውን ጊዜ የክርስቶስን ማንነት ትርጉም ባዶውን ለማስቀረት የማይፈታተን ልክ አበይት ቅዱሳን የላቁ አስተማሪዎች ፈለግ የሚከተል ነው ብለዋል።

የቲዮሎጊያ ሊቅ ልክ እንደ አንድ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማራማሪ ተፈጥሮን አብጠርጥሮ ለማወቅ በተፈጥሮ ላይ ያለው ወደ ላይ የሚመጥቀውን የእግዚአብሔር ህላዌ ምልክት ወደ ጎን በማድርግ በአእምሮአዊ ምርምር ብቻ በመታመን እንደሚያደርገው የማወቅ ሂደት ሳይሆን፣ መጽሓፍ ቅዱስን በጥንቃቄ የሚያጠና ልክ ሰብኣ ሰገልን የመራው ኮከብ በመመልከት እና በመከተል ወደ ወደ እግዚአብሔር ሕላዌ ለመቅርብ እና ለመስገድ ታልሞ የሚፈጸም ምርምር ነው ብለዋል። ብዙ ሊቃውንት መሲሕ የት እንደተወለደ ሊነግሩን ይችላሉ፣ ነገር ግን እንዲከተሉት መጠራታቸው በውስጣቸው የሚናገረው ድምጽ ያማያዳምጡ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ይኸንን ድምጽ ካላዳመጡ መሲሕ ሕይወታቸውን አይለወጥም ልባቸውንም አይነካም፣ ስለ መሲሕ መግለጫ ሊሰጡ ይችላሉ መግለጫው ግን ለሕይውታቸው ሕንጸት ሳይሆን ይቀራል። በዘመናችን አበይት የቲዮሎጊያ ሊቃውንት እና ተመራማሪዎች የእምነት አስተማሪዎች ብዙ ነገር የሚያስተምሩን መጽሐፍ ቅዱስን ጠንቅቀው የሚያውቁ የማዳን ታሪክ የሚያስተምሩ፣ ነገር ግን ኢየሱስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ የእግዚአብሔር ሚስጥር ማእከል መሆኑ ለማየት ለመገንዘብ ያልቻሉ ዓይናቸውን ወደዚሁ ሚስጢር ሳያቀኑ የቀሩ ብዙ ናቸው።

የታሪክ ኢየሱስ ገኖ፣ ተወለደ እንደማንኛውን ሰው ምድራዊ ሕይወቱን ፈጽሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ የሚለው ሳይሆን፣ የእምነት ኢየሱስ ታክሎበት በእምነት በተለወጠ ቲዮሎጊያ መመራት ይኖርበታል። የቤተ ክርስትያን ታሪክ ብዙ ታላላቅ የቤተ ክርስትያን እና የቲዮሎጊያ ሊቃውንት የእምነት አብነት የሆኑ ሰፊ እና ጥልቅ እንዲሁም ትልቅ በሆነው የእግዚአብሔር ሚስጢር ፊት አነስተኛነታቸው ዝቅተኛነታቸው አናሳ መሆናቸው የተገነዘቡ ትህትና ተሞልተው እውነትን ዘንድ ለመድረስ ጥረት ያደረጉ በታሪክ ያለፉ እንዳሉ ያስተምረናል፣ ስማቸውን ለመዘርዘርም ይቻላል።

ልክ እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ዮሓንስ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ትሁታን፣ በጥበብ የተካኑ ነገር ግን ዝቅተኛነታቸውን በሚገባ ተረድተው፣ ትህትናን ተላብሰው የትህና አብነት ማለትም የእግዚአብሔርን ሚስጢር ለመረዳት ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለብን የሚያስተምሩ ናቸው፣ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ለማየት ከፈልግን ዕውሮች መሆናችንን ማየት ለማወቅ ከፈለግን እንደማናውቅ ማወቅ ይገባናል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.