2009-12-02 14:21:08

አንጎላ፣ የፖለቲካ አካላት ቸልተኛነት


የአንጎላ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እንዲመሩ የተመረጡት የሉባንጎ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጋብሪኤል ምቢሊንጉዌ የአንጎላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለማኅበራዊ ሰላም እና ብልጽግና ለሰው ልጅ መከበር እና ለፍትሕ የምታቀርበው ጥሪ RealAudioMP3 የአገሪቱ የፖሊቲካ አካላት ችላ እያሉት ናቸው በማለት፣ በአገሪቱ እየተስፋፋ ያለው ሙስና አድልዎ የሴራ ሃይማኖቶች ጉዳይ አገሪቱን ለከፋው ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ብሎም ኤኮኖሚያዊ ችግር እያጋለጠ መሆኑ ጠቅሰው ይህ አይነቱ ለዘርፈ ብዙ ችግር የሚያጋልጠው ጉዳይ መፍትሔ እንዲያገኝ የፖለቲካ አካላት እና መንግሥት በርትተው መንቃት እንደሚገባቸው ቤተ ክርስትያን ለምታቀርበው ጥሪ ሰሚ ጆሮ መስጠት ይኖርባቸዋል ካሉ በኋላ፣ የአገሪቱ የፖሊቲካ አካላት ሁሉም ለማለት ይቻላል የክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸው፣ ሆኖም ግን የክርስትናው እምነት የሚጠይቀው የግበረ ገብ እና የስነ ምግባር ሕይወት የማይከተሉ ነው የሚመስሉት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.