2009-12-02 14:19:24

ብፁዕ ካርዲናል ዣል ዊስ ታውራን በኢንዶነዢያ


የኢንዶነዢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገውን ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. RealAudioMP3 የጀመሩት የኢንዶነዢያ ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው ዛሬ ፈጽመዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ታውራን በዚህ በካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ከተለያዩ የካቶሊክ ማኅበርሰብ የተለያዩ የምስልምና ሃይማኖት መሪዎች፣ ብሎም ካገሪቱ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት እና ምሁራን ጋር መገናኘታቸው ሲገለጥ፣ ስላካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሓዋርያዊ ጉብኝቱ አወንታዊ ነበር ካሉ በኋላ፣ ለኢንዶነዢያ ብፁዓን ጳጳሳት እና ካህናት በማበረታታት የሚሰጡት ሓዋርያዊ አገልግሎት እንዲቀጡልበትም በማሳሰብ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ልዩ ሰላምታ እና ቡራኬ ጭምር ማድረሳቸው ጠቅሰው፣ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው የጋራ ውይይት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ስለ ጉድይ የሚመለከተውን መመሪያ መርህ በማድረግ እንዲቀጥሉበትም አደራ ማለታቸውም ገልጠዋል።

ኢንዶነዢያ ሰፊ አገር የተለያዩ ጎሳዎች እና ኅብረ ሃይማኖት ያለው ማኅበርሰብ አቀፍ መሆኗ ገልጠው፣ ከተለያዩ ሦስት አንድ የካቶሊክ እና ሁለት የእስላም ሃይማኖት አበይት መናብርተ ጥበብ አስተዳዳሪዎች እስተማሪዎች እና ተማሪዎች ጋር ተገናኝተውም መወያየታቸው ጠቅሰው፣ በዚህ አጋጣሚም የመናብረተ ጥበብ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ሃይማኖታዊ ፖለቲካዊ ነክ ጉዳዮች በውይይት መድረክ ቀርቦ በመረዳት መቀራረብ ሰላም መከባበር የመሳሰሉት እሴቶች ለማጎልበት አይቢ ፍላጎት እንዳላቸው ቀርበው ለመገንዘብ መቻላቸው አረጋገጠዋል።

ሁሉም በእውቀት ለማደግ የሃይማኖቶች ልዩነት በመረዳት ከዚህ አንጻር መቀራረቡን ፈር ለማስያዝ በተለያዩ ሃይማኖት ምእመናን ያለው ፍላጎት እና ሁሉም ለአገር እና ለሕዝብ ጥቅም ብቻ ማተኮር የሁሉም ፍላጎት መሆኑ መገንዘባቸው እና ለካቶሊክ ብፁዓን ጳጳሳት በወር አንድ እሁድ በሃይማኖቶች መካከል ለሚደረገው ውይይት የሚስተነተንበት እና ይኸንን በማሰብ የሚጸለይበት ዕለት ሆኖ እንዲቀደስም ተጨባጭ ሀሳብ ማቅረባቸው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.