2009-12-02 14:18:07

ቅዱስ አብታችን ሮማ የሚገኘው የካሪታስ ማእከል ይጎበኛሉ


ቅዱስ አባታችን ርሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 14 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ ሮማ ስታዚዮነ ተርሚኒ አቅራቢያ የሚገኘው የኢጣሊያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር እንደሚጎበኙ፣ የኢጣሊያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 የካሪታስ ማኅበር ድረ ገጽ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

ቅዱሱ አባታችን የካሪታስ የድኾች መርጃ ማእከል ሓዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ለድኾች ቅርብ መሆናቸው እና እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. የኤውሮጳ ኅብረት የሚያካሂደው የጸረ ድኽነት ዘመቻ በመደገፍ ሲሆን፣ ይህ ማእከል የዛሬ 20 ዓመት በፊት በአባ ልዊጂ ዲ ሊየግር የተቋቋመ በሮማ ከተማ የሚገኙት መጠለያ የሌላቸው መጠለያ በመስጠት እና የምግብ እና የሕክምና እርዳታ በማቅረብ ለኛ ቢጤዎች ሰብአዊ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ሲገለጥ፣ ር.ሊ.ጳ. የሮማ ሊቀ ጳጳሳት እንደ መሆናቸውም መጠን የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች በየአገረ ስብከቶቻቸው የካሪታስ ግብረ ሰናይ ያነቃቁ ዘንድ የሚያሳስብ ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደሚሆን ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.