2009-11-30 14:10:38

የኢጣሊያ ብፁዕና ጳጳሳት ምክር ቤት


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት የሚከበረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቅ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ RealAudioMP3 ለኢጣሊያ ሕፃናት መልእክት ማስተላለፋቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርጥE ክርስቶስ መሠረት ለሕፃናት የሚሰጠው የእምነት ትምህርት ያጠቃለለ የተደረሰው መጽሓፍ ለሁሉም ቁምስናዎች በማሰራጨት፣ ይህ መጽሓፍ ለሕፃናት የልደት በዓል ምክንያት ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው ገጸ በረከት መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ባስተላለፉት መልእክት በመጥቀስ፣ ሕፃናት የሕፃን ኢየሱስ ታሪክ ጠንቅቀው እንዲያውቅ ቁምስናዎች እንዲሁም ቤተሰቦች አቢይ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማሳሰብ፣ እግዚአብሔር አብ ለምን አንዱን የሚወደውን ልጁን ለኛ አሳልፎ እንደሰጠ ስናስተነትን ቀድሞ በአእምሮአችን የሚብሰለሰው ሐሳብ ኢየሱስ ሕፃንን የሚመለከት ነው፣ ስለዚህ ሕፃናት በእግዚአብሔር ዘንድ ምንኛ አቢይ ሥፍራ እንዳላቸው የሚያስገነዝብ የማዳን ታሪክ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.