2009-11-30 14:08:56

የሩዋንዳ የብሩንዲ እና የኮንጎ አቢያተ ክርስትያን


የሩዋንዳ የብሩንዲ እና የዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ የጋራው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ማኅበር 25ኛው ዓመተ ምሥረታ በሶስቱ አገሮች ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በደመቀ መንፈስዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብሮች RealAudioMP3 አማክኝነት እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. መከበሩ ተገለጠ።

በዓሉ ምክንያት በማድረግ ጳጳሳዊ የፍትሕ እና የሰላም ምክር ቤተ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ራፋኤለ ማርቲኖ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሓቅ የተሰኘቸው አዋዲት መልእክት ማእከል ያደረገ ለሶስቱ አግሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ማኅበር አስተምህሮ ለመስጠት እንዲሁም የካቶሊክ የስነ ሃይማኖት ትምህርት መስጫ እና የፍልስፍና እንዲሁም የቲዮሎጊያ እና የተለያዩ የስነ እውቀት ዘርፎች መስጫ የኮንጎ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ የመጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ ለማኖር ወደ ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ እንደሚሄዱ እና የሶስቱ አገሮች አቢያተ ክርስትያን ኢዮቤል ዓመት ምክንያት የሚቀርበው መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ ተገልጠዋል።

ይህ በንዲህእ እንዳለም እዚህ በቫቲካን በተካሄደው ሁለተኛው ይፋዊው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ የተሳተፉት ሲኖዶሱ ያወጣው የፍጻሜ ሰነድ መሠረት በማድረግ የሶስቱ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ነገ የሚጀመር የሁለት ቀን ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.