2009-11-30 14:07:20

የሩሲያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያሪ


የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር የመገናኘቱ ግኑዳይ ተስፋኛ መሆኑ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የመመሪያ ክፍል RealAudioMP3 ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል የሰጡት መገልጫ በመጥቀስ ያሰራጨው ዜና የጠቀሰው ሎ ሶርቫቶረ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አስታወቀ።

ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ ዘርፎች እና እንዲሁም የተለያዩ የፖለቲካ ርእዮት በተለይ የልቅ ፍጆት ባህል የሚያስፋፋው አሉታዊ ባህል የሚያስከትለው መዘዝ ለመከላከል እና ይኸንን ጎጂ ባህል ለመዋጋት በሚደረገው መንፈሳዊ እና ባህላዊ ጥረት በጋራ በመተባበር ለመሥራት እንደሚችሉ እና ሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ግብረ ገብ ለማስፋፋት እና እንዲሁም በሁሉም ዘንድ እንዲከበር በዚህ በምንኖርበት ዘመን የክርስትናው ባህል እንዲከበር ክርስትያን ማኅበርሰብ የክርስትናው ወንጌላዊ እሴቶች በመከተል እምነቱ እንዲመሰክር በማድረጉ ረገድ ተባብረው ለመሥራት እንደሚችሉ የተረጋገጠ መሆኑ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ማሳወቃቸው፣ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ያረጋገጣል።

ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል የሞስኮ እና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ሆነው በማገልገል ላይ በነበሩበት ወቅት ከር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር ሶስት ጊዜ መገናኘታቸው አስታውሰው፣ በተለይ ደግሞ እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር በግል መገናኘታቸው እና እንዲሁም ሌሎች እዚህ በቫቲካን ያካሄዱዋችው ግኑኝነቶች በመዘከር፣ በሁለቱ አቢያተ ክርስያን መካከል ያለው ግኑኝነት የሚያረካ መሆኑ ገልጠው፣ በተለይ የግብረ ገብ ሕይወት በማስፋፋት እና የክርስትናው ባህል በመንከብከብ ረገድ ተባብሮ ለመሥራት እንደሚቻል ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.