2009-11-30 14:04:17

ቤተሰብ ትንሿ ቤተ ክርስትያን


ክርስትያን ማኅበርሰብ ለቅዱስ መስቀል ያለውን ፍቅር ለመመስከር ያቀደ ቤተሰብ ትንሿ ቤተ ክርስትያን የተሰኘው የካቶሊክ ማኅበር ያነቃቃው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ትላትና RealAudioMP3 መከናወኑ ተገለጠ።

ይህ ሮማ ከሚገኘው ከአዲስ ቤተ ክርስትያን አደባባይ የተነሳው መንፈሳዊው የእግር ጉዞ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመድረስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ልክ እኩለ ቀን ባሳረጉት ማርያማዊ ጸሎት እና በሰጡት አስተምህሮ በመሳተፍ የተጠናቀቀ ሲሆን። የዚህ የካቶሊክ ማኅበር መንፈሳዊ አባት ስተፋኖ ታርዳኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ክርስትያን ማኅበርሰብ የተዘጋ መሆኑ ቀርቶ ባደባባይ በመውጣት ሀሳቡን በመግለጥ ለቤተ ክርስትያናቸው ለወንጌል ለቅዱስ መስቀል ያለውን ፍቅር በይፋ በመግለጥ፣ ጸረ የክርስትያን ባህል የሚነሱት አመለካከቶች እና ውሳኔዎች በጸሎት እና በመንፈሳዊ ትጋት መወጣት ብቻ ሳይሆን፣ ባደባባይ በመውጣት በመንፈሳዊ የእግር ጉዞ አማካኝነትም፣ የክርስትናው እምነት በይፋ በመግለጥ ላይ እንደሚገኝ በማብራራት፣ በአሁኑ ወቅት ባንዳንድ አገሮች የክርስትናው እምነት እሴቶች በይፋ እና በምታገለግልበት ማኅበራዊ መድረክ መመስከሩ አስፈሪ እየሆነ መምጣቱ ቢታወቅም እምነትህ በሁሉም መድረክ መመስከር ተገቢ እና ኃላፊነትም መሆኑ የመሰከረ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ነበር ብለዋል።

መንፈሳዊው የእግር ጉዞ ማንንም የሚቃወም ሳይሆን የወንጌልን ፍቅር የሚመሰክር እምነት ሰላም ፍቅር እንጂ የውጥረት የጥላቻ መንስኤ ሊሆን እንደማይችል የሚያረጋግጥ መንፈሳዊ ተግባር ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.