2009-11-30 14:02:12

በካቶሊክ ክርስትያን እና የአንድነት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ግኑኝነት


እ.ኤ.አ. ባለፈው ህዳር 21 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ እና የውህደተ አንግሊካን ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ RealAudioMP3 መካከል የተካሄደው ግኑኝነት የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ግኑኝነት በበለጠ እንዲጠናከር ያሳሰበ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ህዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዓለም አቀፍ የውይይት ድርገት በመገናኘት የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት በሚቀጥለው ዓመት በአዲስ መንፈስ ይከናወን ዘንድ መስማማታቸው የቅድስት መንበር መገልጫ ይጠቁማል።

ይህ በአዲስ መንፈስ እንዲከናወን ከወዲሁ የታቀደው የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት፣ ሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ግብረ ገብ በተመለከተ የሚሰጡት አስተምህሮ የተሟላ ውህደት ያለው እንዲሆን ለማድረግ ቁርጥ ፍቃድ እንደሚደረግ ሲገለጥ፣ ይኸንን አዲሱ የጋራው ግኑኝነት የሚያከናውነው የጋራው ድርገት በቅርቡ እንደሚመለመልም የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.