2009-11-25 14:15:38

የኤድስ መስፋፋታ በዓለማችን


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤይድስ በሽታ ጉዳይ የሚመለከተው ጽ/ቤት፣ ዓለም አቀፍ የጤና ጥበቃ ድርጅት፣ በጋራ ስለ ቀዛፊው የኤድስ በሽታ በማስመልከት አንዲስ ሰነድ ማቅረባቸው ተገለጠ። RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከ 2001 ዓ.ም. እስከ 2009 ዓ.ም. በበሽታው የሚለከፈው ብዛት በ 17% ዝቅ ያለ መሆኑ ሰነዱ በመጥቀስ ከሰሃራ በታች በሚገኘው የአፍሪቃ አግሮች ክልል በሽታው የሚለከፈው ብዛት በ 15%፣ በምስራቅ እስያ በ 25% በደቡብ እና በደቡባዊ ምስራቃ እስያ በ 10% ዝቅ ሲል፣ በተለያዩ አገሮች የኤይድስ በሽታን ለመቆጣጠር የሚሰጠው ህክምና እጅግ ከፍ እያለ መሆኑ ሰነዱ በማስመልከት ይህ ደግሞ በኤይድስ በሽታ የሚሞተው ብዛት እንዲጎድል ማድረግ ለማወቅ ተችለዋል።

ኤይድስ ለመቆጣጠር የሚደረገው የጸረ ኤይድስ ዘመቻ እና የሕክምና ርብርቦሽ አወንታዊ ውጤተ እያስገኘ ቢሆንም ቅሉ፣ ተከስቶ ያለው ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ ለጸረ ኤይድስ ለሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት የሚወጣው ወጪ መንግሥታት እንዲቀንሱ ማስገደዱ ሰነዱ በማስረዳት፣ በጠቅላላ በአለማችን አሁንም 33 ሚሊዮን ሕዝብ የኤይድስ ተህዋስ ተሸካሚ መሆ ኑ እና በ 2008 ዓ.ም. በተህዋሱ የተለከፉት ብዛት ሶስት ሚሊዮን፣ በበሽታው ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሁለት ሚሊዮን መሆናቸው ሰነድ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.